1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ ኦፊሴላዊ ጉብኝት በብሪታንያ

ረቡዕ፣ ግንቦት 17 2003

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአዉሮጳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ቀጥለዋል።

https://p.dw.com/p/RQ2f
ባራክ ኦባማና ዴቪድ ካሜሮንምስል AP

ከትናንት በስተያ ማምሻዉን ብሪታንያ የገቡት ኦባማ፤ ምንም እንኳን ትናንት ይደርሳሉ ተብሎ የታቀደላቸዉ ደማቅ አቀባበል ቀኑ በመስተጓጎሉ ባይከናወንም የተደረገላቸዉ አቀባበል ቀላል እንደማይባል ነዉ የተገለጸዉ። ኦባማ ዛሬ ከብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ጋ የተነጋገሩ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ መወያየታቸዉ ገልጿል። በሊቢያ የጋዳፊን አገዛዝ ለማክተም፤ በሰሜን አፍሪቃና በአረቡ ዓለምም የተቀጣጠለዉን የለዉጥ መንፈስ ለማበረታታት ስለሚኖራቸዉ ሚናም መነጋገራቸዉ ተመልክቷል። የሎንዶኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህን ቀደም ብዬ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ድልነሳ ጌታነህ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ