1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ የስንብት ንግግር

ረቡዕ፣ ጥር 3 2009

ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ንግግሩን ያደረጉትን ከዋይት ሐዉስ ቤተ-መንግሥት ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሴናተርነት ከተመረጡባት ከቺካጎ ነበር። ከስምንት ዓመት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ፊት ያደረጉት የስንብት ንግግር በተደጋጋሚ ጭብጨባ እና አድናቆት የታጀበ ነበር።

https://p.dw.com/p/2VdM4
USA Präsident Barack Obama Abschiedsrede in Chicago
ምስል Picture-Alliance/AP Photo/P. Ma. Monsivais

M M T/ (Beri.wdc) Obama- abschiedsreden - MP3-Stereo

ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ ትናንት እኩለ-ሌሊት ቺካጎ ከተማ ውስጥ የስንብት ንግግር አደረጉ። ከስምንት ዓመት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ፊት ያደረጉት የስንብት ንግግር በተደጋጋሚ ጭብጨባ እና አድናቆት የታጀበ ነበር። ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ሳሉ ወደ ቺካጎ ከተማ እንደመጡ፤ እዚያም ራሳቸውን ፈልገው በስተመጨረሻም ለስኬት እንደበቁ ተናግረዋል። 

«ይህ ከተማ ለውጥ የሚኖረው ማንኛውም የማኅበረሰቡ አካል ሲካተት እና  ተሳታፊ ሲሆን ብቻ እንደሆነ የተማርኩበት ነው። ለስምንት ዓመታት ፕሬዚዳንታችሁ ሆኜ ካሳለፍኩም በኋላ ያ የማምንበት ነው። እምነቴም ብቻ አይደለም። የእኛ የአሜሪካውያን ማንነት የልብ ትርታም ነው፤ ራስን በራስ የማስተዳደራችን ተሞክሮ። ሁላችንም በእኩል መፈጠራችን ያለ እውነት ነው፤ ከማይገሰሱ መብቶቻችን ጋር በነጻነት እና በተድላ እንድንኖር  ከፈጣሪያችን የተሰጠን ጸጋ።»

ታዳሚያኑን «ጥሩ ፕሬዚዳንት አድርጋችሁኛል» ያሉት ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ ምሥጋናቸውን ገልጠዋል። ዩናይትድ ስቴትስ «ልዩ ናት» ሲባል «ገና ከጥንስሱ አንስቶ እንከን አልባ ናት» ማለት እንዳልሆነ፤ ይልቁንስ ሀገሪቱ የመቀየር አቅሟን በማሳየት የተሻለ ሕይወት መምራት እንዲቻል  መደረጉን አጽንኦት ሰጥተውበታል።  በሀገሪቱ የተከሰተው ዘረኝነት አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ማኅበረሰብ ክፍት እንዲሆንም ጥሪ አስተላልፈዋል።  ዲሞክራሲ የሚያብበው ከፓርቲ ወገንተኝነት ውጪ እንደሆነ አሳስበዋል። የ55 ዓመቱ ተሰናባች ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ ወደፊት ማንንም በማይከፋፍል ዲሞክራሲያዊ በሆነ ዘመቻ እንደሚጠመዱ ብሎም ጊዜያቸውን መጽሐፍ በመጻፍ እንደሚያሳልፉ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ ከዘጠኝ ቀናት በኋላ በሪፐብሊካኑ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራምፕ ይተካሉ። 

USA Präsident Barack Obama Abschiedsrede in Chicago
ምስል Reuters/Jonathan Ernst

የዩናይትድ ስቴትስሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ለደጋፊ እና አድናቂዎቻቸዉ ትናንት የስንብት ንግግር አድርገዋል። ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ንግግሩን ያደረጉትን ከዋይት ሐዉስ ቤተ-መንግሥት ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሴናተርነት ከተመረጡባት ከቺካጎ ነበር። እዚያዉ ችካጎ ለተሰበሰቡ ከሐያ ሺሕ በላይ  ደጋፊዎቻቸዉና በመላዉ ዓለም ለሚገኙ አድናቂዎቻቸዉ ባደረጉት ንግግር መስተዳድራቸዉ የምጣኔ ሐብት ኪሳራን በማስወገድ፤ ሥራን በመፍጠር፤ የጥቁርና-ነጮችን ልዩነት በማጥበብ፤ ሀገራቸዉ ከኢራንና ከኩባ ጋር የነበራትን ጠብ በማርገቡ ረገድ ያደረገዉን ጥረትና ያስገኘዉን ዉጤት አዉስተዋል። ለሥራቸዉ ስኬት ደጋፊዎቻቸዉ ላደረጉላቸዉ ትብብር አመስግነዋልም። የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ተጨማሪ ዘገባ አለዉ።

መክብብ ሸዋ

ማንተጋፍት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ