1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ የአላስካ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2007

ኦባማ በዚሁ ጉብኝታቸው በእግር እንዲሁም በጀልባ ተጉዘው በዓየር ንብረት ለውጥ መጠኑ እየቀነሰ የሄደውን የአላስካ የበረዶ ክምችት ተመልክተዋል ።የችግሩ ሰለባ የሆኑ የአላስካ አሳ አጥማጆችን እንዲሁም የጎሳ መሪዎችን አነጋግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1GQD5
USA Barack Obama in Alaska
ምስል Reuters/J. Ernst

[No title]


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በሰሜናዊ ዩናይትድ ስቴትስ በአላስካ ፌዴራዊ ክፍለ ግዛት የጀመሩትን ጉብኝታቸውን ዛሬም ቀጥለዋል ።የጉብኝቱ ዓላማ በበረዶ ግግር በተሞላው በዚህ አካባቢ የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተላቸውን ተፅእኖዎች አሜሪካውያን ትኩረት እንዲሰጡት ማድረግ መሆኑን ዋይት ሃውስ አስታውቋል ። ኦባማ በዚሁ ጉብኝታቸው በእግር እንዲሁም በጀልባ ተጉዘው በዓየር ንብረት ለውጥ መጠኑ እየቀነሰ የሄደውን የአላስካ የበረዶ ክምችት ተመልክተዋል ።የችግሩ ሰለባ የሆኑ የአላስካ አሳ አጥማጆችን እንዲሁም የጎሳ መሪዎችን አነጋግረዋል ። በሌላ በኩል አሜሪካ በአካባቢው የነዳጅ ዘይት ፍለጋ እንዲካሄድ መፍቀዷ እያነጋገረ ነው ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ