1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ የአፍጋኒስታን እቅድ

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2003

የአሜሪካኑ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ እስከሚቀጥለዉ የአዉሮጳዉያን 2012ዓ,ም ድረስ ሰላሳ ሶስት ሺህ የአሜሪካን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን እንደሚወጡ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/RVQ5
ምስል dapd

ፕሬዝደንቱ ከዚህ ዉስጥ አስር ሺህ ያህሉ በያዝነዉ የአዉሮጳዉያኑ ዓመት 2011 የሚወጡ መሆናቸዉን ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ቅነሳ ብታደርግም ሰባ ሺህ የሚሆኑ ወታደሮች እንደሚኖሯትም ተገልጿል። በሂደትም ዋሽንግተን በአፍጋኒስታን የሚኖራት ተልዕኮ ከወታደራዊ ግዳጅ ይልቅ ወደድጋፍ እንደሚቀየርም ፕሬዝደንት ኦባማ አመልክተዋል።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ