1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦብነግ ዝግጅትና ፍላጎት

ረቡዕ፣ የካቲት 13 2011

ግንባሩ «የመጀመሪያ ምዕራፍ» ባለዉ እርምጃዉ የቀድሞ ታጣቂዎቹን ማሰልጠኛ ጣቢያ አስገብቷል።በቃል አቀባዩ መግለጫ መሠረት ሠልጣኞቹ ከሶማሌ ክልል መስተዳድር ልዩ ኃይልና ከሌሎች የክልሉ የፀጥታ ኃይላት ጋር ይቀየጣሉ

https://p.dw.com/p/3Djnt
Mitglieder der ONLF/Ogaden National Liberation Front
ምስል Getty Images/A.Maasho

(Beri.DD) ONLF´s Next move - MP3-Stereo

 የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ አማፂ ቡድን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ሥለወደፊት ፖለቲካዊ ሥራዉ ከኢትዮጵያ የፌደራልና ከሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አስታወቀ።የግንባሩ ቃል አቀባይ እንደሚሉት ግንባሩ «የመጀመሪያ ምዕራፍ» ባለዉ እርምጃዉ የቀድሞ ታጣቂዎቹን ማሰልጠኛ ጣቢያ አስገብቷል።በቃል አቀባዩ መግለጫ መሠረት ሠልጣኞቹ ከሶማሌ ክልል መስተዳድር ልዩ ኃይልና ከሌሎች የክልሉ የፀጥታ ኃይላት ጋር ይቀየጣሉ።ቃል አቀባዩ ማሰልጠኛ ጣቢያ የገቡትን የቀድሞ ታጣቂዎች ቁጥር መግለፅ አልፈለጉም።

 መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ