1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ማስተባበያና የአብን መልስ 

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011

በአማራ ክልል ሰሞኑን የተከሰተዉ ጥቃት «ኦነግ»  የሚመራው የታጠቀ ሰራዊት የለዉም ይልቁንም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ የያዘና ሌሌ የታጠቀ አካል የፈጠረው ቀውስ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ «አብን» ኮንነዋል፡፡ አብን በበኩሉ እንዲህ ያለው ውንጀላ በአደባባይ የተፈጸመን ወንጀል ለመደባበስ ነዉ ብሎአል።

https://p.dw.com/p/3GVju
Karte Äthiopien englisch

«ኦነግ»  በስፍራው የሚመራው የታጠቀ ሰራዊት የለዉም

በአማራ ክልል ሰሞኑን በተከሰተዉ ጥቃት ላይ እጄ የለበትም ሲል በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውየኦሮሞ ነፃነት ግንባር «ኦነግ»  ገለፀ፡፡ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለዶይቼ ቬለ «DW» እንደተናገሩት «ኦነግ»   በስፍራው የሚመራው የታጠቀ ሰራዊት የለዉም ይልቁንም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ የያዘና ሌሌ የታጠቀ አካል የፈጠረው ቀውስ ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቁ «አብን» ኮንነዋል፡፡ ግንባሩ ይህንን ይበል እንጅ ዜጎች ለሞትና የአካል ጉዳት ብሎም ለከፍተኛ ሽብር የተዳረጉበት ይህን ድርጊት ፈጻሚው ኦነግ ነው በማለት የአካባቢው መስተዳድር አካላት ተናግረዋል፡፡ አብን በበኩሉ እንዲህ ያለው ውንጀላ በአደባባይ የተፈጸመን ወንጀል ለመደባበስ የተደረገ ስም ማጥፋት እንጅ እኛ በሰላማዊ ሁኔታ የምንታገል ነን ብሏል፡፡ የችግሩ ዋና ምንጭ በስለጣን ላይ ያለው መንግስት ህግን ማስከበር ያለመቻል ነው ብሎታል፡፡


ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ