1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦፌኮ ባለሥልጣናት የክስ ሂደት

ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2008

ችሎቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ተከሳሾቹ በሌሉበት ነው ። የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት 22ቱ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት እንዲገለፅም ችሎቱ አዟል ።

https://p.dw.com/p/1Ilr8
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

[No title]


የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ነኛ ወንጀል ችሎት በጉርሜሳ አያና መዝገብ የተከሰሱት እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸው ተከሳሾች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ዛሬ ትዕዛዝ አስተላለፈ ። ችሎቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ተከሳሾቹ በሌሉበት ነው ። የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት 22ቱ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት እንዲገለፅም ችሎቱ አዟል ። ተከሳሾች የመቃወሚያ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ሂደቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዘገባ አለው ።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ