1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ አቤቱታና ምርጫ ቦርድ

ሰኞ፣ የካቲት 9 2007

የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ ፣ ምርጫ ቦርድ በቴሌቪዥን በሰጠው መግለጫ ፓርቲው ምልክት ወስዶ እጩዎቹን ግን አላስመዘገበም ማለቱን አግባብነት የሌለው ሲል ወቅሷል።

https://p.dw.com/p/1EcRb
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ እጩዎችን አላስመዘገበም ሲል ባስተላለፈው ዜና ስህተት መፈፀሙን አስታወቀ። የምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደምሰው በንቲ ስህተቱ በማግስቱ በዜና እወጃ እንዲታረም መደረጉንም ለአዲስ አበባው የዶቼቬለ ዘጋቢ ተናግረዋል። የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ ፣ ምርጫ ቦርድ በቴሌቪዥን በሰጠው መግለጫ ፓርቲው ምልክት ወስዶ እጩዎቹን ግን አላስመዘገበም ማለቱን አግባብነት የሌለው ሲል ወቅሷል። ሆን ተብሎ የተደረገ ባለው በዚህ የተሳሳተ ዜና ምክንያትም አባላቱና ደጋፊዎቹ ውዥንብር ውስጥ መውደቃቸውንም ፓርቲዉ አስታውቋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ