1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከርሰ ምድር ዉሃ ብክለት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004

በገፀምድርም ሆነ በከርሠ ምድር የሚገኘዉ ዉሃ በሠዉ ሠራሽ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮም ሊበከል የሚችልበት መንገድ እንዳለ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ለዚህም በዉሃ አካላት ዉስጥ ከሚፈለገዉ በላይ የተለያዩ ንጥረነገሮችን መካከት አንዱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/15Cv3
ምስል CC/Staff Of Hope

የቅመማዉ ሳይንስ የሃይድሮጂን እና የኦክስጅን ዉህደት ዉጤት ነዉ ሲል ይተነትናል ንፁህ ዉሃን። ዉሃ በሠዎችና እንስሳት እንቅስቃሴ እና ተግባራት የመበከል እክል እንደሚገጥመዉ ሁሉ በተፈጥሮም ንፅህናዉን ለጠበቅ መጠናቸዉ የበዛ ንጥረነገሮች በዉስጡ ሲይዝ ብክለት ነዉ።

በቀን ሁለት ሊትር ዉሃ መጠጣት ለጤና መልካም እንደሆነ የሚሰጠዉ ምክር እንዳለ ሆኖ የሚጠጣዉን ዉሃ አስተዉሎ መጠጣቱ ይመከራል። በኢንዱስትሪ በሰለጠነዉ ዓለም ዉሃ ዋነኛ ንግድ እንደመሆኑ ዉስጡ የያዘዉ የንጥረነገር መጠን እየተዘረዘረ፤ በቤተ ሙከራ ገብቶ ጥራቱም እየተፈተሸ ደረጃ ይሰጠዋል። በአዳጊዉ ዓለም ፅድቁ ቀርቶ እንዲሉ ጉሮሮ ማራሻ የሚጠጣዉም ጉልበት ሳያደክም በተገኘ ሊባል ቢችልም፤ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የገፀ ምድርም ሆነ ከርሰ ምድር ዉሃ ትኩረትን ይሻል። ዉሃ የቅንጦት ሸቀጥ አይደለምና። የተፈጥሮ ክስተት እሳተ ጎመራ ያስከተለዉ ብክለት ሳያንስ ሰዉሰራሹ ብክለት መፍትሄ ይሻል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ