1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከባቢ አየር ለዉጥን ለመጠበቅ የአመጋገብ ባህልን መለወጥ

ዓርብ፣ ኅዳር 25 2002

የፊታችን ሰኞ በኮፐን ሃገን በሚጀመረዉ የከባቢ አየር ለዉጥ ጉባኤ የአለማችን ሙቀት መጨመር እና የምግብ ልምዳችን «ጥቂት ስጋ፣ ጥቂት ሙቀት» በሚል ቃል ትናንት በአዉሮጻ ፓርላማ ዉይይት መካሄዱ ተገልጾአል።

https://p.dw.com/p/KqV8
ምስል AP

የዉይይቱ አላማ የአየር መለወጥን ሂደት ለመግታትና ለመቋቋም ሃላፊነቱ ያለዉ በአገሮችና መንግስታት ብቻ ሳይሆን በየደራጃዉ ባሉ ማህበረሰቦች እና ግለሰቦች ጭምር መሁን ለማስገንዘብ እንደሆነ ተገልጾአል። የተናጋሪዎቹ ዋና መልክት የእንስሳት እርባታ ኢንዱስትሪ የእንስሳት የምግብ ዉጤቶች በተለይም ስጋ ለጤና ብዙ የማይበጅ እና ምርቱም የምግን ዉጤትን የሚፈልግ ከመሆኑም በተጨማሪ የአየር ንብረት መለወጥ አስተዋጽኦ ያለዉ በመሆኑ ሰዎች የአመጋገብ ባህላቸዉን በመለወጥ እና የስጋ ፍጆታቸዉን በመቀነስ አለማችንን ብዙ ከመሞቅ ሊጠብቋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተመልክቶአል ዝርዝሩን ገበያዉ ንጉሴ ከብረስልስ

ገበያዉ ንጉሴ/ አዜብ ታደሰ/ ሸዋዩ ለገሰ