1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከብቶች ጤና፤ በአፍሪቃ ቀንድ

ማክሰኞ፣ ጥር 25 2002

የጀርመን ድንበር የለሽ የእንስሳት ሃኪሞች ማኅበር Tierärzte Ohne Grenzen በአዉሮጳዉያኑ 1991ዓ,ም የተመሰረተ የሙያ ማህበር ነዉ።

https://p.dw.com/p/LpnW
ምስል picture-alliance/ dpa

በሃኖቨር የእስሳት ህክምና ማሰልጠኛ ተማሪዎች አማካኝነት የተቋቋመዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ይህ ድርጅት በምሥራቅ አፍሪቃ በተለያዩ አገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻል፤ የእንስሳቶቻቸዉንም ጤንነት በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከዚህም ሌላ ለአርብቶ አደሮቹ የተሻለ ዉጤት የሚያስገኙ የከብት ዝርያዎችን በማዳቀል የሚያገኙት ጥቅም እንዲሰፋ እየረዳ ነዉ። ሰሞኑን በሰሜናዊ ሶማሊያ ራስ ገዝ ግዛት ፑንትላንድ ከአንድ መቶ ለሚልቁ አርብቶ አደሮች ወተትና አይብ፤ እንዲሁም ስጋቸዉን በገፍ ለመጠቀም የሚያስችሉ ፍየል ዘሮችን አከፋፍሏል።

Sophie Grenery

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ