1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኩኩዩ ማህበረሰብ ባህል፣ ኬንያ

ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2001

ዛሪ የባህል መድረካችን ከኢትዮጽያ ምንም ያህል ሳንርቅ ዉቅያኖስ ሳናቋርጥ አድማስ ሳንሻገር አጎራባች ወደሆነችዉ ወደ ኬንያ እንዘልቃለን። በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን ስለኬንያዉያን ባህል በተለይም ስለ ኩኩዩ ማህበረሰብ ባህል በጥቂቱ ያወጉናል።

https://p.dw.com/p/I7M9
ማሳይ፣ ኬንያምስል picture-alliance/ dpa
ኢትዮጽያዉያን እና ኬንያዉያን የቆየ የወንድማማችነት ታሪክ አላቸዉ በስራ አልያም በተለያዩ ምክንያቶች ኢትዮጽያዉያን ሲከፋቸዉ ፈጥነዉ የሚሄዱባት ኪንያ ሆና መቆየትዋ ኬንያዉያን ደግሞ ለግጦሽ ሳር ፍለጋ ወይም ዉሃ ለማጠጣት ጎራ የሚሉባት ኢትዮጽያ ህዝቦችዋ ባህልን ተዋዉቀዉ ይኖራሉ ምንም እንኻ በቋንቋ አንድ ባንሆንም ። ነገርን ነገር ያነሰዋል እንዲሉ አንድ ኢትዮጽያዊ በስራ ምክንያት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሄዶ ሳለ ኬንያዊት ወዶ ፍቅሩን በአስተርጓሚ ከገለጸ በኻላ በርግጥ እኔና አንቺ አልተወያየንም ፍቅር በአስተርጓሚ በመልክት አይሆንም ሲል ገጥሞአል፣ ተዜሞአልም አሉ፣ ሙዚቃዉን ማህደራችን ባናገኘዉም፣ በሱ ምትክ አንድ ከኬንያ ያገኘነዉን ሙዚቃ ይዘናል፣ በዛሪዉ ዝግጅታችን ከሶስት አስርተ አመታት በላይ በኬንያ ኑሮአቸዉን ያደረጉ፣ ወይዘሮ ስለአገሩ ባህል እንዲያከፍሉን ጋብዘናል ከዝግጅቱ ጋር አዜብ ታደሰ መልካም ቆይታ