የኩዌት የምሕረት አዋጅ
ሐሙስ፣ ጥር 17 2010ማስታወቂያ
የኩዌት መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ በግዛቱ ለሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎች አንድ ወር የሚቆይ የምሕረት አዋጅ ደነገገ።እስከመጪዉ የካቲት አካጋማሽ ድረስ በሚቀየዉ ደንብ መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ተወላጆች አንድም ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ ማዉጣት አለያም ወደ ሐገራቸዉ መመለስ ይችላሉ።ኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን አዋጁን በደስታ ቢቀበሉትም የጊዜዉ ማጠር ግን ብዙ እንዳሳሰባቸዉ ይናገራሉ።
ነብዩ ሲራክ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ