1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኪርጊስታን ወቅታዊ ሁኔታ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 1 2002

በህዝባዊ አመፅ የተገለበጡት የኪርጊስታኑ ፕሬዝዳንት ኩርማንቤክ ባክየቭ ከሥልጣን የመውረድ ሀሳብ እንደሌላቸው አስታወቁ ። ሆኖም ህዝባዊው አመፅ ሲባባስ ከመዲናይቱ ከቢሽኬክ ለመውጣት የተገደዱት ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን ከያዘው ከጊዜያዊው አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/Ms4p
ምስል AP
በሌላም በኩል የኪርጊስታን የሽግግር መንግስት በአመጹ የተገደሉትን ዜጎች ለማሰብ ከዛሬ ጀምሮ የሁለት ቀናት ሀዘን አውጇል ። ፕሬዝዳንቱን ለማውረድ በተካሄደው አመፅ የተገደሉት ዜጎች የቀብር ስነ ስርዓትም ዛሬ ተካሂዷል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ