1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካሜሩን ቀውስ እና ለድርድር ፍንጭ የሰጠው የፖል ቢያ ንግግር

ቅዳሜ፣ መስከረም 3 2012

የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከረዥም ጊዜ በኋላ ለአገራቸው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። በፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ ተናጋሪ ክልሎች መካከል ባለ ቅራኔ የምትናጠውን አገር የሚመሩት ቢያ እንዲህ በይፋ ለሕዝባቸው ንግግር ማድረግ አላስለመዱም። ሰውየው ለካሜሩናውያን ንግግር የሚያደርጉት በአመት ሶስት ጊዜ ብቻ ነው።

https://p.dw.com/p/3PbqH
Kamerun Präsident Paul Biya
ምስል picture-alliance/AP Photo/Lintao Zhang

የካሜሩን ቀውስ እና ለድርድር ፍንጭ የሰጠው የፖል ቢያ ንግግር

የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከረዥም ጊዜ በኋላ ለአገራቸው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። በፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ ተናጋሪ ክልሎች መካከል ባለ ቅራኔ የምትናጠውን አገር የሚመሩት ቢያ እንዲህ በይፋ ለሕዝባቸው ንግግር ማድረግ አላስለመዱም። ሰውየው ለካሜሩናውያን ንግግር የሚያደርጉት በአመት ሶስት ጊዜ ብቻ ነው።

የ86 አመቱ ፖል ቢያ በወርሐ የካቲት ለወጣቶች ንግግር ያደርጋሉ። ቀሪዎቹ ሁለት ንግግሮች የካሜሩን ብሔራዊ ቀን ሲከበር እና በአዲስ አመት የሚያደርጓቸው ናቸው። ባለፈው ማክሰኞ ግን ይኸን ልምዳቸውን ተቃርነው ለሕዝባቸው በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት የተላለፈ ንግግር አድርገዋል። ንግግራቸው እንግሊዘኛ ቋንቋ በሚናገረው የካሜሩን ክፍል የተቀሰቀሰውን ፖለቲካዊ ቀውስ የተመለከተ ነበር።

ባለፉት ሶስት አመታት ከካሜሩን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች እና የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች በተደጋጋሚ ተጋጭተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚጠቁመው መገንጠልን በሚያቀነቅኑት ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ግጭት በትንሹ 1850 ሰዎች ሳይገደሉ አይቀርም።

ፖል ቢያ ያደረጉት ንግግር በአገራቸው ፖለቲከኞች እና ተንታኞች ዘንድ አመኔታ የማግኘቱ ነገር እርግጠኛ ቢሆንም የካሜሩንን ቀውስ ለመፍታት ተጨባጭ ምክረ-ሐሳብ አቅርበዋል። የፖለቲካ ነውጥ በበረታባቸው የአገሪቱ ክፍሎች ሰላም እና መረጋጋት እንደሚያሻቻው መረዳታቸውን የገለጹት ቢያ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።

በዛሬው የትኩረት በአፍሪካ መሰናዶ ይልማ ኃይለሚካኤል የፕሬዝዳንት ፖል ቢያን ንግግር ይቃኛል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ