1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካምፓላው ጥቃትና የአፍሪካ ቀንድ ፈተና

ረቡዕ፣ ሐምሌ 7 2002

ባለፈው እሁድ ምሽት የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት በአፍሪካው ቀንድ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ምን ሊሆን ይችላል? በቀጠናው የአክራሪዎችን መጠናከር ያሳያልን?

https://p.dw.com/p/OJAU
ምስል AP

ባለፈው እሁድ ምሽት በኡጋንዳ ካማፓላ በደረሰው የቦምብ ጥቃት የ76 ሰዎች ህይወታ መጥፋቱ ይታወሳል። ለጥቃቱ አልሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል። የፖለቲካው ተንታኞች በዚሁ የአልሸባብ ጥቃት ዙሪያ የቀጠናውን መጻዒ ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል እየገለጹ ነው። በለንደኑ ቻታም ሀውስ ተቋም የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ሳሊ ሂሊ አልሸባብ ከሶማሊያ ምድር እየተሻገረ ጥቃት መሰንዘር መጀመሩ እየተጠናከረ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ሲሉ የአለም አቀፉ የግጭት ቡድን የአፍሪካ ፕሮግራም ሃላፊ ኢጄ ሆክዶረን የሶማሊያ ዘመቻ ያለውጤት በዚሁ ከቀጠለ ቡሩንዲና ኡጋንዳ ጦራቸውን ለማስወጣት መገደዳቸው አይቀርም ይላሉ። ሁለቱንም በማነጋገር መሳይ መኮንን ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ