1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካናዳ መንግሥት የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ

ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2009

የካናዳ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ። በካናዳ መንግሥት ድረ ገጽ ላይ የወጣዉ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያን ባጠቃላይ የሚመለከት ማሳሰቢያ እንደሌለዉ በመጠቆም፤ ባለለዉ አስጊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ዜጎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

https://p.dw.com/p/2irY7
Kanada Fahne
ምስል Getty Images/V. Ridley

ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳስቧል፤

 በዚሁ መሠረትም ወደ ኤርትራ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ አዋሳኝ የድንበር አካባቢ ፈፅሞ እንዳይሄዱ ሲያስጠነቅቅ፤ ወደ ኬንያ የድንበር አካባቢ እና ኗሪዎች ከፀጥታ ኃይላት ጋር ያላቋረጠ ግጭት ዉስጥ ናቸዉ ወዳለዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ደግሞ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ዜጎቹ እንዳይሄዱ አሳስቧል። ዜጎቹ እንዳይሄዱ ያሳሰበበትን አካባቢ በተናጠል በመዉሰድም አሉ ስላላቸዉ የፀጥታ ስጋቶችም ዘርዝሯል። ይህን ማሳሰቢያ አልፈዉ የሚሄዱ የካናዳ ዜጎችም ኃላፊነቱ የራሳቸዉ እንደሚሆን አጥብቆ አሳስቧል። ከቶሮንቶ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽን ስለጉዳዩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አክመል ነጋሽ /ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ