1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካንሰር ምርመራ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ መስከረም 30 2004

በካንሰር የተጠቁ ወገኖችን ቁጥር ኢትዮጵያ ዉስጥ ይሄን ያህል ነዉ፤ በየዓመቱም በዚህ ያህል ቁጥር ይጨምራል ብሎ ለመናገር፤

https://p.dw.com/p/RqNN
ምስል picture alliance/dpa/dpaweb

ለዚህ የሚረዳ ምዝገባ እስከዛሬ ባለመካሄዱ ባይታወቅም፤ ሰዎች ስለጤናዉ ችግር ያላቸዉ ግንዛቤ እያደገ በመምጣቱ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ ቁጥሩ ጨምሮ እንደሚታይ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ለህክምናዉ እንዲረዳ ሊደረጉ የሚገባቸዉ ምርመራዎን በሚመለከት ታዲያ ወጪዉ ከፍተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ምርመራዉ አገር ዉስጥ ለማከናወን የሚያስቸግር የምርመራ ዓይነትም መለያየቱ ታማሚዎቹ በቀላሉ መፍትሄ እንዳያገኙ ስለሚያደርግ፤ ለህልፈተ ህይወት የመዳረግ እድል የሰፋ ነዉ። የዕለቱ ጤናና አካባቢ መሰናዶ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መደረግ ስለተቻለዉ የካንሰር ህመም ምርመራ ዓይነት የሚለን ይኖረዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሠ