1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካንኩኑ የአየር ንብረት ጉባኤና ተስፋዉ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 14 2003

የተመድ ዓለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ የፊታችን ሰኞ በሜክሲኮ ካንኩን ከተማ ይከፈታል።

https://p.dw.com/p/QGK3
ያለፈዉ ዓመት ታህሳስ ወር፤ የጎብኚዎች መስህብ የሆነዉ የቻይና ግዛት በተበከለ አየር ጭጋግ ተሸፍኖምስል AP

ይህ ጉባኤ እንደታቀደለት ከሄደ ከሁለት ዓመታት በኋላ እንደሚያከትም የሚታወቀዉን የኪዮቶን ስምምነት ሊለካና የሚችል የጋራ ዉል በአገራት መካከል ይደረሳል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። ባለፈዉ ዓመት በዚሁ ወቅት በዴንማርክ ኮፐንሃገን የተካሄደዉ ተመሳሳይ ጉባኤ ብዙ እንደተወራለት ሳይሆን መቅረቱ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ቢሆንም፤ ዘንድሮም ተስፋ ባለመቁረጥ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች የተመድ አባል አገራት ወደሚያግባባቸዉ ነጥብ እንዲደርሱ በየደረጃዉ ግፊት እያደረጉ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ