1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካዉካሰሱ ግጭት ሰበብና እዉነተኛዉ ምክንያት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 27 2000

የቲቢሊሲን ቤተ-መንግሥት የተቆጣጠሩት ወገኖች በዉጪዉ ግፊት፥ በሥልጣን ጥማት ይሆን በዘር ወይም በሌላ ምክንያት ያን ጅልነት ገና ያኔ ፈፀሙት

https://p.dw.com/p/FA3R
ትንሹ ዉጤትምስል AP
ሐምሌ ማብቂያ የኢራቅ አፍቃኒስታንን የእልቂት-ግድያ ዜና ደፍልቆ፥ የቤጂንግ ኦሎምሊክን ድግሥ ድምቀት አፍዝዞ የመገናኛ ዘዴዎችን ገፅ-ሥርጭት ያጣበበዉ የካዉካስ ወታደራዊ ግጭት ለመቆም በርግጥ ሁለት ሳምንት አልፈጀበትም።የፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ እሰጥ-አገባ ወታደራዊዉ ግጭት ከሚካሔድበት ጊዜ ይበልጥ ንሮ መቀጠሎ በርግጥ ግራ ነዉ።የቃላት እንኪሥላንቲያዉ፥ የዲፕሎማሲዉ ጥልፍልፍ፥ ጡንቻ ፍተሻዉ ከቲቢሊሲ፥ አብካዝ፥ ኦሲቲያ፥ ወይም ከቲቢሊሲ ሞስኮ ይልቅ የሞስኮ-ዋሽንግተን ብራሥልስ መሆኑ ደግሞ ካዉካሰስ ወትሮም ሰበብ እንጂ ምክንያቱ ሌላ መሆኑን እየመሰከረ ነዉ።የሰበብ-ምክንያቱ እንዴትነት ያፍታ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ አብራችሁኝ ቆዩ።