1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያዉ የጎሳ ግጭት መንስኤ

ሰኞ፣ ሰኔ 30 2006

የኬንያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መንግሥትን በመንቀፍ ህዝብ ለተቃዉሞ እንዲወጣ ጥሪ ያቀርባሉ። በሀገሪቱ የሚታየዉ የፖለቲካ ልዩነትና መቃቃር፤ የጎሳ ግጭት ቀዉስ አጥልቶበታል። በኬንያ በሚገኙት የተለያዩ ጎሳዎች መካከል የሚታየዉ ቀዉስ እየሰፋ መጥቶአል።

https://p.dw.com/p/1CXU4
Kenia Prozess gegen William Ruto Kriegsverbrechen Symbolbild
ምስል picture-alliance/AP Photo

በዛሬዋ ዕለት በኬንያ «ሳባ ሳባ ዴይ» በመባል የሚታወቅ ልዩ ቀን ነዉ። ዕለቱ በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ,ም በኬንያ የሚገኙ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ፤ የዝያን ግዜዉን የኬንያ ፕሪዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይን በመንቀፍ ህዝብ በገፍ አደባባይ የወጣበት ነበር። ያኔ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ከተደረገ በኃላ ዘጋጁ በኃላ፤ በሁለተኛዉ ዓመት በኬንያ የመጀመርያዉ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መካሄዱ ይታወቃል። የዝያን ግዜዉ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ምርጫዉን አሸንፈዉ ስልጣናቸዉን እንደያዙ ቆይተዋል። በየኬንያዉ የጎሳ ግጭት መንስኤ በሚልር ርዕስ የዶቼ ቬለዉ ፊሊፕ ዛንደር ያዘጋጀዉን ዘገባ አዜብ ታደሰ እንዲህ ታቀርበዋለች።

ይህን ታሪካዊ ቀን በማስታከክ የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እና የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዴንጋ፤ በያዝነዉ ዓመት ለኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሀገሪቱን አሳሳቢ ችግርና የደህንነት ሁኔታን በማስመልከት ብሄራዊ ዉይይት እንዲደረግ ሲሉ ማስጠንቀቅያና የግዜ ገደብ ሰጥተዉ ነበር። በሌላ አነጋገር ይህ ተፈፃሚ ካልሆነ ራይላ ኦዴንጋ በኬንያ በ1990 ዓ,ም እንደተጠራዉ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃዉሞ፤ መዲና ናይሮቢ ላይ ህዝብን ለንቅናቄ እንደሚጠሩ ነዉ የዛቱት። በአሁኑ ግዜ በጋዜጠኝነት ሞያ በማገልገል ላይ የሚገኙት፤ በኬንያ በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸዉ ታዋቂና በቀድሞ ግዜ ፕሬዚዳንቱን በመተቸታቸዉ ለተደጋጋሚ ግዜ ወህኒን የጎበኙት፤ ኮጊ ዋ ዋምዊር ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳቡን አደባባይ የመግለፅ መብት አለዉ፤ ሲሉ ይናገራሉ፤

Kenia Raila Odinga
ራይላ ኦዲንጋምስል RODGER BOSCH/AFP/Getty Images

« ማንኛዉም የፖለቲካ ፓርቲ በነፃነት አደባባይ የመሰብሰም መብት አለዉ። ግን ፕሬዚዳንቱን ዉኃ ባለመኖሩ ጢሞትን የሚላጩት ያለ ዉኃ ነዉ ቢባል የማይሆንና ያልተለመደ ነገር ነዉ የሚሆነዉ። ይህ ነገር ቢከሰት ነገሩ ሁሉ ድብልቅልቁ ነዉ የሚወጣዉ »

በኬንያ በነበረዉ የፖለቲካ ግጭት፤ ጥሎት የሄደዉ ጥቁር የህሊና ጠባሳ ማኅበረሰቡ የሚረሳዉ አይደለም። በጎርጎረሳዊዉ 2007 ዓ,ም በተካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫና ዉጤት አወዛጋቢ ነበር። በእጩ ነት የቀረቡት ራይላ ኦዲንጋ በዚያንግዜዉ ፕሬዚዳንት፤ ማዊ ኪባኪ ከተሸነፉ በኃላ ፤ የሁለቱም ወገን ደጋፊዎች በመካከላቸዉ ግጭትን ጀመሩ፤ ከዝያም የጎሳ ግጭቱ ተፋፋመ። በቀዉሱ ከ1200 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወሳል። እንደ ጋዜጠኛ ኮጊ፤ በርካታ ኬንያዉያን በዛሪዋ ዕለት ማለት በጎርጎረሳዉያኑ ሰኔ ሰባት፤ በሀገሪቱ ዳግም ብጥብጥ ይጫራል ብለዉ ይሰጋሉ። በምዕራባዊ ኬንያ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ፤ የጎሳ ግጭትን የሚያጭር ወረቀት ከተበተነ በኃላ፤ በአካባቢዉ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ ብጥብጥ ቢነሳ ቦታዉን ጥሎ ለማምለጥ ሻንጣቸዉን ሸክፈዉ በተጠንቀቅ እንደሚገኙም ዘገባዎች ጠቁመዋል።

የራይላ ኦዲንጋ የፖለቲካ ንቅናቄ፤ የብዙኃኑን ጥያቄን ስለማያካትት፤ በበርካታ ኬንያዉያን ዘንድ የኦዲንጋ እንቅስቃሴ ግልፅ አይደለም። በኬንያ ማሲንዴ ሙሊሮ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ጉዳይ ታዛቢዉ ብራይን ሲንጎሮ ዋንያማም በዚህ ኃሳብ ይስማማሉ፤

« ሁኔታዉ የመሪነት ስልጣን ለመያዝ ብቻ ነዉ ። ይህን ጥያቄ ኦዲንጋም ሆነ መንግሥትእንዲሁም ተቃዋሚዎች አቅርበዉታል» ብራይን በመቀጠል፤ የኬንያን ብሔራዊ የፀጥታ ሁኔታን በማስጠበቅ ጉዳይ አስመልክቶ መንግሥት ይላሉ ፤ « መንግሥት ብሄራዊ ዉይይትን ሳያደርግ፤ ከፍተኛ የቁጣ ድምፅን እና ህዝብን መሰብሰብ ይፈልጋል። አንድ ችግርን ለመፍታት በሚደረግ ጥረት፤ ሳባ ሳባ የተሰኘዉን ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ አያስፈልገንም»

በኬንያ በደህንነት እና ፀጥታ ጉዳይ የሚደረገዉ ዉይይት እና ክርክር ፤ ግንቦት አጋማሽ የኬንያ የባህር ዳርቻ በሆነችዉ ፕኬቶኒ ከተማ በአልሸባብ የጥቃት ሰንሰለት በተከታታይ ስትደበደብ ዉይይቱ እና ክርክሩ ዳግም በአዲስ ጀመረ። ለጥቃቱ በሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉ የአሸባብ ቡድን ኃላፊነቱን ቢወስድም፤ ጥቃቱ ከደረሰ ከአንድ ቀን በኃላ፤ በአካባቢዉ ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ፤ እኔ ከፈለኩበት ኩኩዩ ጎሳ ላይ የጣሉት ብትር ነዉ ሲሉ የኬንያዉ ፕሪዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መናገራቸዉ ይታወሳል። የፕሪዚዳንት ኬንያታን ንግግር የሰሙት የፖለቲካ ጥናት ተቋም ባልደረባ ማርጌት ሄልቬግ ቦቴ፤ ነገሩን አደገኛ ብለዉታል፤ « ፕሪዚዳንት ኬንያታ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ ግንቦት ወር ይህን በተናገሩ ግዜ ፤ በፒኩቱኒ ያለዉ የሰፈራ ሁኔታ ትልቅ ሂስ ቀርቦበታል። መንግሥት እስካሁን በዚህ ጉዳይ ያለዉና የተገበረዉ ነገር የለም። ይህ ንግግር በመንግሥትና በፓርላማዉ የማህደር መሳብያ ዉስጥ ሳይከፈት መፍትሄና መልስ ሳይሰጥበት ተድበስብሶ የተቀመጠ ነገር ነዉ»

Kenia Wahlen Unruhen Demonstration der Opposition in Kisumu
ምስል AP

የኬንያ ወደብ አቅራብያ የሚገኙ አካባቢዎች የሚታየዉ የጎሳ ግጭት ሀገሪቱ ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀች ከጎርጎረሳዉያኑ 1963 ዓ,ም ጀምሮ የሚደረግ ነገር ነዉ። የዝያን ግዜዉ ፕሪዚዳንትና የአሁኑ ፕሬዚዳንት የኡሁሩ ኬንያታ አባት ጆሞ ኬንያታ አካባቢዉ ላይ የፒኪቶኒን ጎሳ ፈቃድ ሳይጠይቁ፤ ነዋሪዎችን አስፍረዋል። ይህ ሁኔታ የጎሳ ግጭትን መቀስቀሱን የፖለቲካ ጥናት ተቋም ባልደረባዋ ማርጌት ገልፀዋል።

ዛሪ በኬንያ ታስቦ ዋለዉ ሳባ ሳባ ዴይ፤ በጎሳ መካከል ግጭት እንዳልታየበት ተስፋ ይደረጋል። በዶቼ ቬለ የፊስቡክ ገጽ ላይም ከ 200 የሚበልጡ የስዋሂሊ ቋንቋ መረሃ- ግብርን ተከታታዮች ዛሪ ሰኞ ሰላማዊ ቀን ይሆናል ሲሉ፤ የሰላም መልክታቸዉን፤ ተስፋቸዉን አስተላልፈዋል።

Margit Hellwig-Boette
ማርጌት ሄልቬግ ቦቴምስል picture-alliance/dpa

የኬንያ ወደብ አቅራብያ የሚገኙ አካባቢዎች የሚታየዉ የጎሳ ግጭት ሀገሪቱ ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀች ከጎርጎረሳዉያኑ 1963 ዓ,ም ጀምሮ የተከሰተ ነገር ነዉ። የዝያን ግዜዉ ፕሪዚዳንትና የአሁኑ ፕሬዚዳንት የኡሁሩ ኬንያታ አባት ጆሞ ኬንያታ አካባቢዉ ላይ የፒኪቶኒን ጎሳ ፈቃድ ሳይጠይቁ፤ ነዋሪዎችን አስፍረዋል። ይህ ሁኔታ የጎሳ ግጭትን መቀስቀሱን የፖለቲካ ጥናት ተቋም ባልደረባዋ ማርጌት ገልፀዋል።

በጎርጎረሳዉያኑ 2007 ዓ,ም በኬንያ ቀዉስ ከጋረደዉ ምርጫ በኃላ፤ የመሪት ድልድል አጣሪ ኮሚሽኑ ርዕስ ነበር። ማርጌት ሄልቬግ በጎርጎረሳዉያኑ 2013 ዓ,ም ባቀረቡት የማጠቃለያ ዘገባ በፒኪቶኒ የተደረገዉ የሰፈራ መረሃ-ግብርን በተመለከተ በኬንያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ሂስን አቅርበዋል።

ዛሪ በኬንያ ታስቦ ዋለዉ ሳባ ሳባ ዴይ፤ በጎሳ መካከል ግጭት እንዳልታየበት ተስፋ ይደረጋል። በዶቼ ቬለ የፊስቡክ ገጽ ላይም ከ 200 የሚበልጡ የስዋሂሊ ቋንቋ መረሃ- ግብርን ተከታታዮች ዛሪ ሰኞ ሰላማዊ ቀን ይሆናል ሲሉ፤ የሰላም መልክታቸዉን፤ ተስፋቸዉን አስተላልፈዋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ