1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ም/ቤት አባላት ገቢ

ሐሙስ፣ ጥር 30 2005

ከአንድ ወር በኋላ ብሔራዊ ምርጫን የምታካሂድ ኬኒያ፣ የህዝብ ተወካዮቿ በዓለም ከፍተኛ ደሞዝ ከሚያገኙ የፓርላማ አባላት ተርታ ይመደባሉ። ሆኖም ብዙ ኬኒያውያን ለፖሊቲከኞቹ የሚሰጠውን ጥቅማ ጥቅምና ከፍተኛ ደመወዝ እየታዘቡ ይነቅፉታል።

https://p.dw.com/p/17ZFY
A
ምስል picture-alliance/dpa

ኬኒያውያን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም አፍሪቃውያን በፖሊቲከኞቻቸው ደመውዝ ላይ ቅሬታ ያሰማሉ። ኢሳቤላ ባወር የዘገበችውን ገመቹ በቀለ ያቀርበዋል።

የኬኒያ ፓርላማ አባላት በወር ከግብር ነጻ የሆነ በጥቅሉ 9000 ዩሮ ወይም ቢያንስ 180,000 ብር ያገኛሉ። ይህ የጀርመን የፓርላማ አባላት ከሚያገኙት የላቀ ነው። በተጨማሪ፣ ተወካዮቹ 6000 ዩሮ የኪስ አበል፣ ነጻ የመኖሪያ ቤት፣ ነጻ ስልክ መደወያ እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን ያገኛሉ። ከዚህም ውሳኔ የደረሱት በራሳቸው ነው። ተወካዮቹ ባለፈው ጥር ለፓርላማ ባቀረቡት ረቂቅ ህግ በአገልግሎት ዘመናቸው መጨረሻ ለያንዳዳቸው 80,000 ዩሮ አበል እንዲሰጣቸው ፈልገው ነበር። ከዚህም ሌላ፣ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት በመንግስት እንዲፈጸም፣ ጠብመንጃ የታጠቀ ጠባቂ እንዲመደብላቸው፣ የዲፕሎማት መታወቂያ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። ለዛ ነበር በቅርቡ ኬኒያውያን ይህን ከልኩ ያለፈ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኙ ፖሊቲከኞችን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት። አንቶኒ ቶሽ በመዲናዋ ናይሮቢ የተካሄደውን ሰልፍ ካቀናጁት ሰዎች አንዱ ነው። ለዚህ ዓይነቱ ስግብግብነት የፓርላማ አባላቱ ብቻ ሳይሆኑ መራጮችም ተጠያቂ ናቸው ይላል፤

«የምንመርጠው እንድንመርጣቸው የሚከፍሉንን መሪዎች ነው። ችሎታ ያለውን መሪ ሳይሆን ገንዘብ የሚሰጥህን መሪ ትመርጣለህ። እነኚህ ሰዎች እንድትመርጣቸው ገንዘብ ይሰጡሃል። ፓርላማ ሲገቡ የመጀመሪያ አጀንዳቸው ላንተ ያወጡትን ገንዘብ እንዴት መልሰው እንደሚያኙ ማሰላሰል ነው።»

ተወካዮቹ በአገልግሎት ዘመናቸው መባቻ አበል እንዲሰጣቸው ያቀረቡት የህግ ረቂቅን ፕሬዚዳንት ሚዋይ ኪባኪ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣናቸውን ተጠቅመው ውድቅ አድርገውታል። ለርሳቸው ግን ሥልጣናቸውን ሲለቁ ከ200, 000 ዩሮ በላይ አበል እንዲከፈላቸው ጠይቀው ነበር። በርግጥ ክፍያው ሳይጨምርም፣ ከዓለማችን ከፍተኛ ደምወዝ ከሚከፈላቸው መሪዎች ግንባር ቀደም ናቸው። በዓመት 600, 000 ዩሮ ያገኛሉ፤ ይህም የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርከል ከሚያገኙት በሁለት እጥፍ ይበልጣል።

በአፍሪካ፣ ኬኒያ ብቸኛዋ ሀገር አይደለችም። በናይጀሪያም ፖሊቲከኞች ከፍተኛ ደመዎዝ ያገኛሉ። እንደ ኬኒያ ሁሉ በናይጀሪያም ደመወዝ ከጥቅም ጋር ይያያዛል። ባለስልጣናቱ የሚገኙትን ደመወዝ ራሳቸውን ለማደላደል፣ ዘመዶቻቸውን ለመርዳትና የቅርብ ሰዎቻቸውን ለመጥቀም ይገለገሉበታል ይላሉ ጋዜጠኛና የናይጄሪያ ፖሊቲካ ባለሙያ ሃይንሪች ቤርግሽተሬሰር። በተጨማሪም ገንዘቡን ወደ ፊት ስልጣናቸውን ሲለቁ ለመጠቀም ያከማቻሉ፣

«ይህ ማለት፣ እነኚህ የፖሊቲካ መደቦችና አመራሮች ባጠቃላይ ለብቻቸው የራሳቸውን ህይወት መምራት ይችላሉ። በዚህ ከዘይትና ጋዝ ምርት በሚገኝ ትልቅ ገንዘብ ምክንያት ከመራጮቻቸው ተለይተው ለራሳቸው የፈጠሩትን ዓለም ማቆየት ይችላሉ።»

ሆኖም በእውነተኛ ዲሞክራሲ ተወካዮች ከመራጮቻቸው ተለይተው መስራት አይችሉም ይላሉ ባለሙያው ቤርግሽተሬሰር። የናይጄሪያ ፓርላማ አባላት ከሌሎች ሀገራት የፓርላማ አባላት ጋር ሲተያዩ፤ ለሥራቸው የተሻለ ምቹ አገልግሎት ቢኖራቸውም በዲሞክራሲ ግን ከሌሎች ሀገራት ተሽለው አይታዩም። ለዛ ነው በብዙ የአፍሪቃ ሀገራት ድምጽ ሰጪው ህዝብ ፖሊቲከኞች የሚያገኙትን ከፍተኛ ደሞዝና ቦታ ይገባቸው እንደሆነ የሚጠይቁት። ለምሳሌ የጋና ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍና በማህበራዊ መገናኛ መረቦች ቅሬታዎቻቸውን ያሰማሉ። የደቡብ አፍሪቃ የፓርላማ አባላት ከፍ ያለ ደመወዝ በማግኘት ከአፍሪቃ አራተኛ ደረጃ ላይ ናቸው። ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በወር 14,000 ዩሮ ያገኛሉ። እያንዳንዱ የፓርላማ አባልም ቢያንስ 6000 ዩሮ ያገኛል። የሀገሬው ህዝብ ግን በአማካይ በወር የሚያገኘው 40 ዩሮ ብቻ ነው።

ከደቡብ አፍሪቃ፣ ከናይጄሪያና ኬኒያ ቀጥለው የጋናና ናሚቢያ የፓርላማ አባላት ከአፍሪቃ ከፍተኛ ደመወዝ ያገኛሉ። ከአፍሪቃ ዚምባብዌና ቤኒን ለፓርላማ አባሎቻቸው ዝቅተኛውን ደመውዝ ይከፍላሉ። በቤኒን፣ ፕሬዚዳንቱ በወር የሚያገኙት ደመወዝ 2000 ዩሮ ብቻ ነው።

Mwai Kibaki, Kenias neuer Präsident
ፕሬዝደንት ሙዋይ ኪባኪምስል picture-alliance/dpa
Kenia Nairobi Parlament Archiv
የኬንያ ምክር ቤትምስል picture-alliance / dpa

ኢሳቤላ ባወር

ገመቹ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ