1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ባለስልጣናትና ICC

ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2005

የአዲሱ የኬንያ ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ ጠበቆች ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ችሎት በኬንያታ ላይ የመሠረተዉን ክስ እንዲያነሳ ሰሞኑን ጠይቀዋል። ጠበቆቹ ይህን ያቀረቡት ባለፈዉ ሳምንት የፍርድ ቤቱ ጠበቆች በተመሳሳይ የተከሰሱትን የፍራንሲስ ሙታዉራን ክስ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ካደረጉ በኋላ ነዉ።

https://p.dw.com/p/182Ej
ምስል picture-alliance/dpa

የመንግስት ሠራተኛ የሆኑት ሙታዉራ ላይ ለቀረቡ መረጃዎች ዋነኛ የተባሉ ምስክር ለመቅረብ ባለመቻላቸዉ ሊጣል ግድ እንዳለ የICC ጠበቆች አመልክተዋል። ከዚህ በመነሳትም የኬንያታ ጠበቆች ICC ያቀረበዉን ማስረጃ አጠራጣሪነት በመጥቀስ ክሱ ዉድቅ እንዲሆን አመልክተዋል። እንደዋና አቃቤ ህግ ፋቱ ቤንሱዳ ገለፃ ምስክርነት የተቆጠሩት አብዛኞቹ በህይወት የሉም፤ አለያም ደብዛቸዉ ጠፍቷል። በተመሳሳይም በኬንያምክትልፕሬዝደንት ዊልያምሩቶላይይመሰክራሉተብሎየተጠበቁእማኝሃሳባቸዉንመለወጣቸዉካለፈዉምርጫጋበተገናኘየቀረበዉንክስአወሳስቦታል እየተባለ ነዉ።ሩቶእንደኬንያታሁሉከአምስት ዓመታት በፊት ከተካሄደዉ ምርጫ ማግስት የተደራጀወንጀልበማነሳሳትተከሰዋል።ሁለቱምየኬንያየአሁን ከፍተኛ ባለስልጣትየቀረበባቸዉንክስዉድቅበማድረግስማቸዉከወንጀሉእንዲጸዳመማፀን ይዘዋል።አቃቤህጉኬንያታኬንያዉስጥየተደራጀጥቃትበመፈፀምለሚታወቀዉሙኑጊለተሰኘዉቡድንገንዘብከፍለዉአመፁበተባባሰበትወቅትለኪኩዩጎሳከለላእንዲያደርግሳያደርጉእንዳልቀሩይጠረጥራሉ።ኬንያታጥርጣሬዉንዉድ አድርገዋል።

Francis Kirimi Muthaura
ፍራንሲስ ኪሪሚ ሙታዉራምስል picture-alliance/dpa

በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ከሶስቱ የዓለም ዓቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ዳኞች ፊት የቀረቡት የፕሬዝደንት ኬንያታ ጠበቃ ስቴቨን ኬይ፤ ለሐምሌ የተቀጠረዉ የደንበኛቸዉ ዶሴ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደመዝገብ ቤት እንዲገባ ይሻሉ። የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤህጎችበሩቶላይይመሰክራሉየተባሉትግለሰብም አለመገኘታቸዉንየሚያረጋግጡከሆነICC አመፁንበማቀነባበርየተጠረጠሩወገኖችንበተጠያቂነትየመያዝአቅሙጥያቄላይእንደሚወድቅነዉየተገመተዉ።የሩቶጠበቃዴቪድሆፐርለምስክርነትይቀርባሉየተባሉትግለሰብናይሮቢላይበጠበቃቸዉአማካኝነት በእማኝነትለመቅረብከእንግዲህእንደማይፈልጉመግለፃቸዉን ለዘጋቢዎች ተናግረዋል።ሆፐርእንደሚሉትምስክሩፍርድ ቤት ቀርበዉ የሃሰትቃልእንዲሰጡማንነቱንባልገለፁትግለሰብግፊትእንደተደረገባቸዉ አመልክተዋል።እሳቸዉእንዳሉትምICC ምስክሮችን በሚከልልበት ህጋዊ መንገድ ማንነታቸዉን የሸሸገዉን ምስክር የኬንያ ጋዜጦች ይፋ አድርገዋል።

Kenia William Samoei Ruto
ዊልያም ሩቶምስል AP

እንዲያምሆኖየICC አቃቤህጎችበዚህጉዳይእስካሁንያሉትነገርየለም።የምስክሮች በጉዳዩ ላይ እማኝነታቸዉን ከመስጠት ወደኋላ ማለት የፍርድ ሂደቱን ሊያራዝም እንደሚችል ተገምቷል። ኬንያዊዉዳኛጎርዶንሙዊኪራበአንድጉዳይላይለምስክርነትየተጠሩእማኞችተመሳሳይነትጉዳዩንእንደሚያወሳስበዉነዉያመለከቱት፤

«ክሱአንድዓይነትከሆነምስክሮች፤አንድዓይነትከሆኑ፤አደጋዉየሚመጣዉእዚያላይነዉ።ፍራንሲስሙታዉራላይበፍርሃትምይሁንበሌላምክንያትምስክርነታቸዉንለመስጠትካልፈለጉ፤በቀጣይምበኬንያታላይለመመስከርፈቃደኛአይሆኑምማለትነዉ።»

የICC ዋና አቃቤ ህግ ፋቱ ቤንሱዳ ትናንት ከፓሪስ ለጋዜጠኞች እንደገለፁት ከሆነ ግን የኬንያታ ክስ ዉድቅ አይደረግም። ቤንሱዳ ያሉት ጥያቄዉ መቼ የሚለዉ ካልሆነ በቀር ለኬንያ ፕሬዝደንትነት የተመረጡት ዑሁሩ ኬንያታ ፍርድ ቤት መቅረባቸዉ አይቀርም። አያይዘዉም ዋና አቃቤ ህጓ ምስክሮች ላይ ከሚፈፀም ማዋከብ በተጨማሪ የኬንያ መንግስት ይህን ጉዳይ ለማጣራት ከኬንያ መንግስት ወገን ትብብር ማጣታቸዉንም ገልጸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ