1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ተቃዋሚ ጥምረት እና አይ ሲ ሲ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 20 2006

በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ፣ በምሕፃሩ አይ ሲ ሲ ክስ የተመሰረተባቸው የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ ችሎት ወደሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ለማድረግ በሀገሪቱ የተጀመረው ጥረት ሳይሳካ ቀረ።

https://p.dw.com/p/1A9FG
Kenya's newly elected President Uhuru Kenyatta attends the Easter Mass at the Saint Austin's Catholic church in the capital Nairobi, March 31, 2013. Kenya's Supreme Court upheld Uhuru Kenyatta's presidential election victory on Saturday and his defeated rival accepted the ruling, helping douse tensions after tribal violence blighted the election five years ago. REUTERS/Thomas Mukoya (KENYA - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል Reuters

ጥረቱ የከሸፈው «ኮዋሊሽን ፎር ሪፎርምስ ኤንድ ዴሞክራሲ» በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ዋነኛው የተቃዋሚው ጥምረት ትናንት አባላቱ የሆኑ ሀገረ ገዢዎች፣ እንዲሁም፣ የብሔራዊ እና ያካባቢያዊ ምክር ቤት ቡድኖች ካካሄዱት ምክክር በኋላ በኬንያውያኑ መሪዎች ላይ በዘ ሄግ ኔዘርላንድስ የተጀመረው የችሎት ሂደት መቀጠል አለበት በሚል አቋሙ በመፅናቱ ምክንያት መሆኑ ተገልጾዋል።
በኬንያ ምክር ቤት የሚወከሉት የተለያዩት ፓርቲዎች እንደራሴዎች የሀገሪቱ ፕሬዚደንት እና ምክትላቸው ችሎት ወደሌላ ጊዜ ይተላለፍ የሚለውን ሀሳብ ያነቃቁት በሀገሪቱ የአንድነቱን ስሜት ለመፍጠር በማሰብ ነበር። ይሁን እንጂ፣ የተቃዋሚዎች ጥምረት «ኮዋሊሽን ፎር ሪፎርምስ ኤንድ ዴሞክራሲ» ትናንት የአምስት ሰዓት ምክክር ካደረገ በኋላ ፣ በኬንያውያኑ ባለሥልጣናት ላይ የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ፣ አይ ሲ ሲ የመሠረተው የክስ ሂደት መቀጠል አለበት በሚል ይዞት በቆየው አቋሙ መፅናቱን የቡድኑ የሕግ ጉዳዮች ተጠሪ ጄምስ ኦሬንጎ አስታውቀዋል።
«አይሲሲን በተመለከተ አቋማችን ግልጽ ነው፣ አልተቀየረም፣ አፅንዖት መስጠት የፈለግነው ነገር ችሎቱ እዚያው ዘ ሄግ መቀጠል እንዳለበት ነው። ገዢው የጁብሊ ፓርቲ ሁኔታውን መለወጥ ከፈለገ፣ ከሮሙ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መውጣት አለበት። ከዚህ ውጭ በየትኛውም የተመድ ደንብም ሆነ ሕግ አባል መንግሥታት የክሱን ሂደት ማራዘም አይችሉም። »
ይሁንና፣ እአአ በ2005 ዓም ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ግጭት የተጎዱት ሰለባዎች ፍትሕ ማግኘት ይችሉ ዘንድ በዚሁ ጥያቄ ላይ ከመንግሥት እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋ በዚያው በሮሙ ስምምነት ማዕቀፍ ገንቢ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ፓርቲው አመልክቶዋል።
የትናንቱን ምክክር የተከታተሉት የፖለቲካ ተንታኝ ባሮን ሺቲሚ እንዳስረዱት፣ የተቃዋሚው ጥምረት ገዢው ፓርቲ ሀገሩን ከአይሲሲ ለማስወጣት የያዘውን ዕቅድ ይተዋል የሚል ተስፋ አሳድሮዋል።
« የዛሬው ስብሰባ ገዢው ፓርቲ ይህን ረቂቅ ሀሳብ ለምክር ቤት ካቀረበ የተቃዋሚው ወገን እንደሚቃወመው መልዕክት ያስተላለፈ ነበር። ለፖለቲካ ጥቅም ነው መባሉ ትክክለኛ አይደለም። በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በወንጀል የተከሰሰ ፕሬዚደንት መኖሩ ጥሩ አይደለም፣ ግን፣ ለኛ ለኬንያውያን ፍርድ ቤቱ ለሀገር ስም እና ክብር በጣም ጥሩ ነው። »
የተቃዋሚው ጥምረት ከትናንቱ ስብሰባው በኃላ በፕሬዚደንቱ እና በምክትላቸው ላይ የተመሠረተውን ክስ በተመለከተ አቋሙን ይቀይራል በሚል ተስፋ ተደርጎ ነበር። የፕሬዚደንት ኬንያታ ችሎት እአአ የፊታችን ህዳር 12 በዘ ሄግ፣ ኔዘርላንድስ ይጀመራል።

Kenyans walk past the parliament building in Nairobi on September 5, 2013. Kenyan lawmakers backed a motion to pull out of the International Criminal Court, an angry snub to The Hague-based tribunal ahead of next week's trial of Vice President William Ruto. The motion "to suspend any links, cooperation and assistance" to the court was overwhelming approved by the National Assembly. AFP PHOTO / SIMON MAINA (Photo credit should read SIMON MAINA/AFP/Getty Images)
ምስል Simon Maina/AFP/Getty Images
Kenya's Deputy President William Ruto speaks with broadcaster Joshua arap Sang (R) in the courtroom before their trial at the International Criminal Court (ICC) in The Hague September 10, 2013. Ruto appeared at the International Criminal Court on Tuesday for the opening of his trial on charges of co-orchestrating a post-election bloodbath five years ago. Ruto and his co-accused, the broadcaster Joshua arap Sang, could face long prison terms if convicted. To the left is defense counsel Karim Khan. REUTERS/Michael Kooren (NETHERLANDS - Tags: CIVIL UNREST POLITICS CRIME LAW)
ምስል Reuters

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ