1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ዘመቻ በሶማሊያና የአሸባብ በቀል

ማክሰኞ፣ ግንቦት 21 2004

የአፍሪቃ ህብረት እና የሶማሊያ ወታደሮች ቁልፍ የሆነች የጦር ሰፈር-አፍጎዬን ከሶማሊያ እስላማዊ አክራሪ ቡድን - አሸባብ ነጥቀው መቆጣጠራቸው ከተገለፀ ገና ጥቂት ቀናት ነው። በአንድ በኩል የአሸባብ ሽንፈት ሲገለፅ በሌላ በኩል አሸባብ ስፍራውን

https://p.dw.com/p/153vh
A fire burns in a clothing stall after an explosion in a shopping complex in Kenya's capital Nairobi, May 28, 2012. A blast struck a shopping complex in Nairobi's business district during Monday's lunch hour, wounding more than a dozen people, but it was not immediately clear what had caused the explosion. Dense black smoke billowed from the badly damaged building and sirens blared as emergency service crews rushed to Moi Avenue, a major road running through the city centre. REUTERS/Johnson Mugo (KENYA - Tags: SOCIETY CIVIL UNREST CRIME LAW)
ምስል Reuters

ለቆ የወጣው በሽንፈት ሣይሆን ስልታዊ ማፈግፈግ መሆኑን አመልክቷል። እንዲሁ ትናንት በኬኒያ ናይሮቢ በፈነዳ ፈንጅ 33 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል። አሸባብ ጥቃቱን ስለማድረሱ በይፋ ባይናገርም፣ ባይወስድም፣ ብዙዎች ተጠያቂ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። በሶማሊያ የኬንያ ጦር የጀመረው ዘመቻንና አሸባብ በምላሹ እየወሰደው ነው የሚባለውን በቀል በተመለከተ ልደት አበበ በፕሪቶሪያ-የደቡብ አፍሪቃ የአለም አቀፍ የፀጥታ ተቋም የፖለቲካ ተንታኝን አነጋግራለች።

የአፍሪቃ ሕብረትና የሶማሊያ ወታደሮች ከሞቃዲሾ ሰሜን-ምዕራብ 30 ኪሎሜትር ፈንጠር ብላ የምትገኘው አፍጎዬን ከአሸባብ ቡድን አስጥለው 400 000 ተፈናቃይ ሱማሊያውያን ይኖሩበት ነበር የተባለውን መሬት በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል። ይህ ትክክል ከሆነ የአፍሪቃ ህብረት በአሸባብ ላይ የያዘውን ዘመቻ አጠናቅሮ መዝለቅ ይችላል ማለት ይሆን?- ፕሪቶሪያ- ደቡብ አፍሪቃ በሚገኘው አለም አቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ISS የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ- ኤንድሩስ አታ አሳሞአ መልስ ሰተውናል።

epa02950295 A burned car is seen at the scene of a car bomb explosion in war-torn Somalia's capital Mogadishu, 04 October 2011. Reports state that more than 50 people have been killed after a vehicle exploded in front of the Ministry of Education building. Al Qaeda-linked Islamic militia al-Shabab has claimed responsibility for the deadly attack. EPA/ELYAS AHMED
ሞቃዲሾ ውስጥ አሸባብ ያደረሰው ጥቃትምስል picture alliance/dpa

« የአፍሪቃ ህብረት ይህንን ቦታ ማስለቀቅ መቻሉ የአፍሪቃ ህብረት ወደፊትም ትግሉን መቀጠል ያስችለዋል ብዬ አስባለሁ። ይህንን ስል የአፍሪቃ ህብረት ከሱማሊያ የሽግግር መንግስት TFG ጋ በመተባበር ሞቃዲሾን ከአሸባብ ለማስለቀቅ ከመቻላቸው በመነሳት ነው። በዚህም የተነሳ የአፍሪቃ ህብረት ነፃ ያደረጋቸውን ቦታዎች ይዞ የመቆየት አቅም አለው ማለት ይቻላል። አንደኛ የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች ቁጥር በቦታው እየጨመረ ነው። ሁለተኛ አሸባብ ቀደም ሲል እንደነበረው ጠንካራ አይደለምና።»

በነዚህ ሁለት ምክንያቶች የተነሳ ለአሸባብ የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮችን መዋጋት አዳጋች ቢያደርገውም ትግሉ ለአፍሪቃ ህብረትም ፈታኝ እንደሚሆን አታ አሳሞአ ይገልፃሉ።

« ቦታውን ይዞ መቆየቱ ፈታኝ ይሆናል።ምክንያቱም ግጭት ሊኖር እንደሚችል መጠበቅ ይኖርብሻል። የአፍሪቃ ህብረት ወታደር መከላከሉ ላይ ነው የተሰማራው እነሱ ደግሞ ማጥቃቱ ላይ ነው። ከመከላከል ይልቅ የአጥቂውን ቦታ መያዝ የተሻለ ነው። ስለዚህ ፈታኝ ይሆናል። ይሁንና የአፍሪቃ ህብረት ኃይል ቦታውን በቁጥጥር ስር እንደሚያውል እጠብቃለሁ።»

**FILE** In a Tuesday Nov. 4, 2008 file photo, Somali militia of Al-Shabab are seen during exercises at their military training camp outside Mogadishu. Islamic fighters now control most of southern and central Somalia, with the crucial exceptions of Mogadishu and Baidoa. Islamic fighters declared Thursday, Nov. 13, 2008, that they will use strict Muslim rules to bring their lawless Horn of Africa country back under control. (AP Photo, File)
እስላማዊ አማፂው ቡድን በሱማሊያምስል dapd

ትናንት በኬንያ ናይሮቢ በተጣለው ፈንጅ ቢያንስ 33 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ይህን መሰሉ ጥቃት ምን ያመላክታል? ኤንድሩስ አታ አሳሞአ « የኬኒያ የፀጥታ ተቋማት ቦንቡ በአሸባብ አካላት መጣል አለመጣሉን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ግን የትናንቱ የናይሮቢ ጥቃት የሚያመላክተው በተለይ ለምን እንደተጣለ ስናይ በኬንያ ላይ የሚጣሉት ጥቃቶች መጠናከራቸውን ነው። ከአሸባብ ይሁን አይሁን አላውቅም። አሸባብ ነው ብዬ ማለት አልፈልግም። ግን ኬንያ ደህንነት አስከባሪዎቿን ማጠናከር ይኖርባታል። ከጥቅምት ጀምሮ በኬንያ መኖሪያ በአሸባብ የሚጣሉት ጥቃቶች አይነት ጨምረዋል። ስለዚህ ኬንያ የሚቻል ከሆነ እነዚህን ቡድኖች ለማስወገድ በአገሪቷ እና በሶማሊያ የፀጥታ ቁጥጥሩን የበለጠ ማጠናከር አለባት።»

እንዲሁም የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚ- ኤንድሩስ አታ አሳሙአ በምስራቅ አፍሪቃ ያለውን የሽብር ጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚቻል ሲያብራሩ፤ « ሽብርን እና ጥቃትን ማሸነፍ ከፈለግን ፤ የሽብር መንስኤዎችን መመልከት ይኖርብናል።ሁለተኛ ደግሞ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡትን ምንም አይነት ስራም ሆነ መኖሪያ የሌላቸውን ወጣቶች ቁጥር መቀነስ ይኖርብናል። ይህንን የአፍሪቃ መንግስታት በስፋት ሊገነዘቡ ይገባል። የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር በጨመረ ቁጥር በአገሪቷ ላይ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በር እየከፈትን መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።»

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ