1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን  የገጠመው ቀውስ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2010

የኬንያ  ገለልተኛ የምርጫ እና ድንበር አካላይ ኮሚሽን፣ በምህፃሩ አኢቢሲ ትናንት ሦስት ከፍተኛ ኮሚሽነሮች ትናንት በፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ለቀቁ።  

https://p.dw.com/p/2wCxV
Kenia Wahlwiederholung | Chef der Unabhängigen Wahlkommission (IEBC) Wafula Chebukati
ምስል picture-alliance/AP Photo/S. Abdul Azim

አ ኢ ቢ ሲ 

ኬንያ እንደ ጎርጎሳዊያን አቆጣጠር ነሐሴ 2017 ያካሄደችው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጠ/ፍርድ ቤቱ ውድቅ ከተደረገ ወዲህ ችግር ላይ ያለው ኮሚሽን አሁን በዚሁ ሰበብ ሌላ ከባድ ቀውስ ውስጥ ገብቷል፡፡ የኮሚሽኑን ምክትል ሊቀመንበር ወይዘሮ ኮንሶላታ ማይና እና ሁለት ከፍተኛ ኮሚሽነሮች ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዲህ በማለት ሊቀመንበሩን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ «በዘፈቀደ በሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ ለግል ክብር፣ ዓላማ እና ለጥቅም ሲባል ከኮሚሽኑ ውስጥ በሚስጢር ሾልከው በሚወጡ መረጃዎች ሳቢያ ተቋሙ ሽባ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ እነዚህ ሁሉ ኮሚሽኑ እና ሠራተኞቹ ሊመሩበት ከሚገባው ስነ ምግባር ጋር የሚጋጩ ናቸው፡፡ ኮሚሽነሮች ለተሾምንለት ዐላማ ብቻ ነው መስራት ያለብን፡፡ በኮሚሽኑ ውሳኔ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ አካላትን አስወግደን ነጻነታችን ማስጠበቅ መቻል አለብን፡፡ ለዚህ ሁሉ ግን ሊቀመንበሩ ብቁ አመራር መስጠት ሳይችሉ ነው የቀሩት» በኮሚሽኑ ሃላፊዎች መካከል ስር የሰደደ ክፍፍል ሰፍኖ የቆየ ቢሆንም ቅራኔው የተባባሰው ግን ሊቀመንበሩ ዋፉላ ቸቡካቲ የኮሚሽኑን ሥራ አስኪያጅ እዝራ ችሎባን ከጨረታ ግድፈት ጋር በተያያዘ ከ10 ቀናት በፊት ከሃላፊነት ካገዱ በኋላ ነው፡፡ የሦስቱ ኮሚሽነሮች መልቀቅ ከተሰማ ጀምሮ የገዥው እና ተቃዋሚው ፓርቲ የፓርላማ አባላት ባልተለመደ ሁኔታ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዋፉላ ቸቡካቲ እና ቀሪዎቹ ሦስት ኮሚሽነሮችም በቶሎ ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው እንዲለቁና አዲስ ኮሚሽን እንዲዋቀር ጠንካራ የጋራ ግፊት ማድረጉን ተያይዘውታል፡፡ በፓርላማው አብላጫ መቀመጫ ያለው የገዥው ጁብሊ ፓርቲ ተጠሪ አደን ዲዋሌ ዛሬ ከቀትር በኋላ ለኬቲኤን ቴሌቪዥን ሲናገሩ ግን ምትክ ኮሚሽነሮችን ለመሾም ፓርላማው የሕግ ክፍተት እንዳለበት ገልጸዋል፤ «አሁን አዲስ ኮሚሸን ለማዋቀርም ሆነ አንድም ኮሚሽነር ቢሆን ለመተካት የምንችልበት ሕግ የለንም፡፡ እናም ፓርላማው በተለይም የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴ ቀጣዩ ኮሚሸን እንዴት እንደሚዋቀር ረቂቅ ሕግ ፈጥኖ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ አጠቃላይ የመረጣ እና ቅጥር ሂደቱ ደሞ 50 ቀናት ያህል ይወስዳል» አደን ዲዋሌ የጠቀሱት የሕግ ክፍተት የተፈጠረው በፓርላማው አብላጫ ድምጽ ያለው ገዥው ጁብሊ ፓርቲ በጥቅምቱ ዳግም ምርጫ ዋዜማ ላይ ከሰባቱ ኮሚሽነሮች አምስቱ ተሰብስበው ውሳኔ ማሳለፍ ይችላሉ የሚለውን የምርጫ ሕግ አንቀጽ በማሻሻል ወደ ሦስት ኮሚሽነሮች ካወረደው በኋላ ባለፈው ሳምንት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ማሻሻያ አንቀጹ ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ነው በማለት ውድቅ ስላደረገው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ በሕጉ መሠረት ሊቀመንበሩ እና ኮሚሽነሮቹ ከሥልጣናቸው ሊነሱ የሚችሉት በፓርላማው የሚቋቋም ልዩ የዳኝነት ቦርድ የምርጫ ሕጉን መተላለፋቸውን የሚያሳይ ጥፋት ካገኘባቸው እና የቦርዱን ውሳኔ ሃሳብም ፕሬዝዳንቱ ከፈረሙበት
ብቻ እንደሚሆን የምርጫ ሕጉ ያዛል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዋፉላ ቸቡካቲ በበኩላቸው የሃላፊዎቹን መልቀቅ የሰሙት ከመገናኛ ብዙሃን መሆኑን በጽሁፍ ባሰራጩት መግለጫ ገልጠው የለቀቁት በመርህ ልዩነት ሳይሆን ሥራ አስኪያጁ በሕግ ተጠያቂ በመደረጋቸው ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያሉት ኮሚሽነሮች ሦስት ብቻ ቢሆኑም ሊቀመንበሩ ግን ከሃላፊነታቸው እንደማይለቁ አጽንዖት ሰጥተው ነው የተናገሩት፡፡ የገዥው ፓርቲ የፓርላማ ተጠሪ አደን ዲዋሌ ግን በሊቀመንበሩ አቋም አይስማሙም፤ «ኮሚሽኑ ቀውስ ውስጥ መግባቱን ገልጸው ዋፉላ ቸኩባቴ የአመራር ቀውስ መፈጠሩን ለሀገሪቱ ማሳወቅ አለባቸው፤ ብቁ አመራር መስጠት እንዳልቻሉ እና ኮሚሽነሮች እና ሴክታሪታሪያቱ በእኔ እምነት ስላጣ በገዛ ፍቃዳዴ ለቅቄያለሁ ብለው ለአዲስ ኮሚሽን መቋቋም በር መክፈት አለባቸው፡፡ ይሄ እንዲያውም መለኮታዊ አጋጣሚ እኮ ነው፡፡ ምክንያቱም ካሁን በፊት ኮሚሽኑን እንደገና ስናዋቅር የኖርነው ምርጫ ሊደርስ አንድ ወይም ሁለት ዐመት ሲቀር ብቻ ነበር»… ከምርጫው በፊት በምህጻረ ቃሉ NASA እየተባለ የሚጠራው በራይላ ኦዲንጋ የሚመራው ተቃዋሚው ብሄራዊ ልዕለ ጥምረት ምርጫ ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር አበክሮ ሲጠይቅ የነበረው ጉዳይ ነው፡፡ የኮሚሽሮቹን መልቀቅተከትሎም በሴኔቱ የተቃዋሚው ናሳ ተጠሪ ጄምስ ኦሬንጎ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ክስተቱ የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታጁብሊ መንግስት ቅቡልነት እንደሌለው እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውም የተጭበረበረ እንደነበር የሚያረጋግጥ ነውብለዋል፡፡ኮሚሽኑን እንደ አዲስ ለማዋቀር ጥሪው የተሟሟቀው ባላንጣዎቹ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ተቃዋሚያቸው ራይላኦዲንጋ በቅርቡ የደረሱበትን ሚስጢራዊ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ በጀመሩበት ማግስት እና ኦዲንጋምእንደ ጎርጎሳዊያኑ አቆጣጠር በቀጣዩ የ2022ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዳግም ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ግምቶችበጠነከሩበት ሰዓት ነው፡፡
ቻላቸው ታደሰ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

Wahlen in Kenia 2017 - Kampagne von Uhuru Kenyatta
ምስል Getty Images/AFP/S. Maina
NASA-Logo
ምስል picture-alliance/dpa/EPA/A. M. Sprecher
Kenia Nairobi Wahlen Stimmenauszählung
ምስል Reuters/T. Mukoya