1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ጦር ዘመቻ በሶማልያ እና የአሸባብ ዛቻ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 2004

በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ትናንት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በጣለው ጥቃት ቢያንስ አምሥት ሰዎች ሲገደሉ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉም ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/Rrmd
ምስል picture alliance/dpa

በመኪና ላይ የተጠመደው ቦምብ የፈነዳው ሁለት የኬንያ ሚንስትሮች ከሶማልያ የሽግግር መንግሥት ባለሥልጣናት ጋ ይወያዩ በነበረበት የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሕንፃ አቅራቢያ ነበር። ጥቃቱ በደቡባዊ ሶማልያ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ ዘመቻ በጀመረው የኬንያ ጦር አንፃር አፀፋ ርምጃ እንደሚወስድ ዛቻ ያሰማው የሶማልያውያን ያማፅያን ቡድን የአሸባብ ሥራ ሳይሆን እንዳልቀረ የሞቃዲሾ ፖሊስ ቃል አቀባይ አብዱላሂ ሀሰን ባሪሴ ገልፀዋል። አሸባብን ባለፉት ጊዜያት ኬንያ ውስጥ በውጭ ዜጎች ላይ ለተካሄዱት ዕገታዎች ተጠያቂ ያደረገችው ኬንያ የሶማልያን መንግሥት ስምምነት አግኝታ ዘመቻውን መጀመሯን ብታስታውቅም፡ በዚሁ ዘመቻ አኳያ በሁለቱም ሀገሮች ውስጥ የተለያየ አስተያየት ነው የሚሰማው።

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ