1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ እና ምክር ቤታዊው ምርጫ መሸጋገረ

ሰኞ፣ ጥር 7 2004

የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ እና ምክር ቤታዊው ምርጫ ወደ መጋቢት ወር እአአ 2013 ዓም እንዲሸጋገር የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።

https://p.dw.com/p/13ka4
ህዝበ ውሳኔ በኬኒያ
ምስል AP

ምርጫው ተሻሽሎ በወጣው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት እንደተጠቀሰው በዚህ ዓመት ነሀሴ ወር መካሄዱ ቀርቶ ወደሌላ ጊዜ መሸጋገሩ፤ በርካታ ኬኒያውያንን እያስቆጣ ነው።

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንታዊ እና ምክር ቤታዊው ምርጫ ወደሚቀጥለው ዓመት መጋቢት ወር እንደሚገፋ ባለፈው ዓርብ ገልፆ፤ ምርጫው በዚህ ዓመት ቀደም ብሎ ሊካሄድ የሚችለው፤ ጣምራው መንግስት እንዲፈርስ ፕሬዚደንቱ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ መስማማታቸውን በጽሑፍ ሲያስታውቁ ብቻ መሆኑን አመልክቶዋል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ