1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ 50ኛ ዓመት የነጻነት ክብረ-በዓል

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 3 2006

ኬንያ የምሥራቅ አፍሪቃ የዕድገትና መረጋጋት ሞተር መሆኗ ነው የሚነገርላት።ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ በሄግ ፤ ኔዘርላንድስ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት፤ ቢከሰሱም፤ አገራቸው፤ እ ጎ አ በ 2010 አዲስ

https://p.dw.com/p/1AY7E
ምስል DW/A. Kiti

ዴሞክራሲያዊ ሕገ-መንግሥት አጽድቃ በመንቀሳቀስ ላይ ናት። በአገሪቱ ፤ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቷል ቢባልም ኤኮኖሚው ከ 5 ከመቶ በላይ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ናት። ኬንያ፤ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ስለተላቀቀችበት 50ኛ ዓመት የነጻነት በዓል፤ የዶቸ ቨለዋ አንድሪያ ሽሚት ያቀረበችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

እ ጎ አ ከ 1895 አንስቶ እስከ ፤ ለ 68 ዓመታት የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበረችው

ኬንያ፤ በ 1950 ዎቹ ዓመታት ኪኩዩዎች ባካሄዱት የአመጽ ትግልና ቅኝ ገዥዎቹም ብርቱ የግፍ ተግባር ከፈጸሙ በኋላ ነበረ ፤ የማይገታ አመጽ መቀጠሉ እንደማይቀር የተገነዘቡት እንግሊዞች፤ እ ጎ አ በ 1963 ግዛቲቱ ነጻ እንድትወጣ የተስማሙት።

ኬንያ፤ በቅርቡ፣ በከፊል ምድረ- በዳማው ሰሜናዊ ግዛቱ በከርሠ-ምድር ሰፊ የውሃ ሀብት እንዲሁም ነዳጅ ዘይት የማግኘቷ ዜና የዕድገቷን ተስፋ ይበልጥ አለምልሞታል። የኬንያ ጦር ሠራዊት፤ በአፍሪቃው ኅብረት ሰላም የማስከበር ተልእኮ በመሳተፍ ላይ ሲሆን ፤ ይህን ለመበቀል አሸባብ፤ ኬንያ ውስጥ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጭካኔ የተመላበት አደጋ ከመጣል አልቦዘነም።

የመጀመሪያው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆሞ ኬንያታ
ምስል AP

ከ60 ከመቶበላይየሚሆኑትኬንያውያንዕድሜአቸውከ24 ዓመትበታችነው።በመዲናይቱበናይሮቢ፤በዛባሉየኢንተርኔትአገልግሎትሰጪቤቶችየሚኮለኮሉወጣትኬንያውያን50ኛውን የነጻነትበዓል በማክበርላይየሚገኙት ስለወደፊቱመጻዔ-ዕድላቸውበመጨነቅብቻሳይሆን በኩራትና በተስፋ መንፈስ ጭምር ነው። ከዛሬው የነጻነት ክብረ በዓል አኳያ ከዜጎችዋ አንዳንዶች የሚሉትን ብናስደምጣችሁ---

«ስሜ ሲቢለ ሙንይካ ነው። መጠኑ እጅግ በዛ ያለ ህዝብ ከድህነቱ ጠርዝ ከፍ ባለ ደረጃ ይኖራል ፤ ያም ሆኖ መኖሪያ ቤት የሌላቸው ጥቂቶች አይደሉም፤ ለወጣቶች በቂ የሥራ ቦታ የለም። አሁን ካሉን የተሻሉ በሙስና የማይዘፈቁ መሪዎች በኖሩን እላለሁ።»

«ጆዋን ኦቺንግ ኦንያንጎ እባላለሁ፤የመገናኛ ብዙኀን ተማሪ ነኝ፤ አገሪቱ በሥነ ቴክኒክ በመራመደ ላይ ናት። በዛ ያሉ ተግዳሮቶች ከፊታችን ተደቅነዋል። ሀገሪቱ በሚገባ አልለማችም። »

ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያታ
ምስል John Muchucha/AFP/Getty Images

«ሳሙኤል እባላለሁ፤ የንብረት አያያዝ ነው ትምህርቴ፣ ከ 50 ዓመት በፊት ከነበሩት ወገኖቻችን ይልቅ እኛ አሁን በታሻለ ሁኔታ እንኖራለን ። ሥነ-ቴክኒክ፤ ዘመናዊ መሳሪያዎችና መረጃዎች ለእኛ ክፍት ናቸው።»

ሴራ ኦባማ ፤ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አያት
ምስል ROBERTO SCHMIDT/AFP/Getty Images

በእርግጥ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ኬንያ ውስጥ እጅግ በመስፋፋት ላይ ነው። ኬንያውያኑም የፈጠራ ችሎታቸውን አዳብረዋል። ለግብርና ፤ ለጤና ጥበቃ ተስማሚ የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘርግቷል። M-Pesa የሚሉት በተንቀሳቃሽ ስልክ(ሞባይል) ለተለያዩ ጉዳዮች ገንዘብ መክፈልና ገንዘብ መላክ የሚቻልበት አገልግሎት እጅግ በመስፋፋት ላይ ነው። እንዲያውም እንደ ካሊፎርኒያው(ዩናይትድ ስቴትስ)የሥነ -ቴክኒክ ማዕከል SILICON VALLEY ኬንያም የአፍሪቃ «ሲሊኮን ሳቫና» የሚል ተቀጥላ ሥም ተሰጥቷታል። «ሳቫና» በብዛት ሰንበሌጥ መሰል ረዣዥም ሣርና አልፎ-አልፎ ቁጥቋጦም ሆነ ዛፍ የሚታይበት ከምድር ሰቅ አካባቢ ፈንጠር ብሎ የሚገኝ የምድር መቀነት መሆኑ ነው)

እ ጎ አ በ 2007 ከተካሄደው ምርጫ ማግሥት አንስቶ በውጤት አጨቃጫቂነት የተነሳ በተፈጠረ ጎሳ ነክ ግጭት ከ 1000በላይ ሰዎች የተገደሉበት ሁኔታ አሁንም በዓለም አቀፉ የጮር ወንጀለኞች መርምሪ ፍርድ ቤት ፋይሉ እንደተከፈተ ነው። ያኔ የተፈጠረው ደም አፋሳሽ ውዝግብ ፣የተለያዩ ብሔራትንና ነገዶችን ያቀፈች ፤ የተባበረች ኬንያን የማደርጀቱ ዓላማ ሳንክ እንዳጋጠመው የታዘቡት «ሳውቲ ኩ» (ጠንካራ ድምፅ) እንደማለት ነው በኪስዋኺሊ፣ የዚህ የወጣቶች ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት፤ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እኅት አውማ ኦባማ፤ እንዲህ ይላሉ---

«እኔ በግል እንደታዘብኩት፤ ኬንያውያን እርስ በርስ በተሻለ ሁኔታ መቀራረብና፣ አንዱ ለሌላው በጎ ማሰብ ይኖርበታል። እንደማየው እርስ በርሳችን እንጨካከናለን ፤ትኁቶች መሆን ይኖርብናል።

ደብረ ኬንያ(Mt.Kenya)
ምስል picture-alliance/dpa

የጎሳ አስተሳሰብን ማስወገድ ይኖርብናል። ስለሀገሪቱ ልማት ስናስብ፤ ምንጊዜም ከአእምሮአችን መጥፋት የሌለበት ጉዳይ፣ ሌሎችን ስንረዳ ፣ ራሳችንን እንደራዳን ሊቆጠር እንደሚገባ ነው። »

አንድሬያ ሽሚት

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ