1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የክሩዝ አዲሱ ገጸ-ባህሪ ለጀርመን ታሪክ ጥፋት?

እሑድ፣ ሐምሌ 8 1999

በአሜሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ መአከል ተደናቂዉ እና በተለያዩ የፊልም ስራዎቹ ታዋቂ የሆነዉ አሜሪካዊዉ የፊልም አክተር ቶም ክሩዝ የተሰጠዉን ገጸ ባህሪ በመላበስ በጀርመን በበርሊን ከተማ የፊልም ቀረጻ ሊጫወት ያሰበዉን የፊልም ትወና እንዳይሰራ ታግዶአል።

https://p.dw.com/p/E0mG
ቶም ክሩዝ/ሽታዉፍንበርግ
ቶም ክሩዝ/ሽታዉፍንበርግምስል AP
ቶም ክሩዝ ይህን ፊልሙን እንዳይሰራ የታገደበት ምክንያት ምንድን ነዉ የዛሪዉ የባህል መድረካችን በቁጥር አንድ ርእሱ ሊያስቃኘን ተዘጋጅቶአል። ሌላዉ ባለፈዉ ሳምንት የአለም ሰባቱ አስደናቂ ቅርሶች በሚል በሊዝበን ፖርቱጋል ዉስጥ ምርጫ ተካሂዶ ሰባት የአለም ድንቅ ቅርሶች ተመርጠዋል። በዚህ ምርጫ በኢትዮጽያ የሚገኙ ጥንታዊ እና አስደናቂዎቹ አብያተ ክርስትያናት ወይም የአክሱሙ ሃዉልታችን ከሰባቱ ምርጥ የአለም ቅርሳት ለመካተት እድል አላጋጠመዉም። እዉነት ቅርሶቻችን ጥንታዊና ማራኪ ሳይሆኑ ቀርተዉ ነዉን? ባለሞያ አነጋግረናል! ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ