1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሌራ ወረርሽኝ በኬንያ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2008

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት መከሰቱ እየተነገረ ነው። የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህንኑ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታን አስመልክቶ ከጥቂት ጊዜ በፊት መግለጫ ማውጣቱ ተሰምቶዋል።

https://p.dw.com/p/1ILOE
Mosambik Kampagne gegen Cholera
ምስል DW/M. Mueia

[No title]

ይህን በተመለከተ በኢትዮጵያ ስላለው የጤና ሁኔታ ለመዘገብ መረጃ በማሰባሰብ ላይ ነን። የጎረቤት ኬንያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲያውም በአንዳንድ የሀገሩ አካባቢዎች የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሰተ ነው ይፋ ያደረገው። ወረርሽኙ ፈጥኖ ሊዛመት ስለሚችልም አስቸኳይ ርምጃ እንዲወሰድ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አሳስቧል። ባንዳንድ የኬንያ አካባቢዎች ገባ ስለተባለው የኮሌራ ወረርሽኝ ኬንያ የሚገኘው ወኪላችን ፋሲል ግርማ በዝርዝሩ ገልጾልናል።

ፋሲል ግርማ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ