1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮርያ ዘማቾች ትዉስታ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2005

የኮርያ የዕርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ዘንድሮ ስድሳ ዓመቱን ያዘ። በኮርያ የእርስ -በርስ ጦርነት ጊዜ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ በመሰለፍ ከደቡብ ኮርያዉያን ጋር የተሰለፉት ኢትዮጵያዉያን፤ የኮርያ ዘማቾች ማህበር በሚል ጥላ ስር ከተሰባሰቡ 20 ዓመት በላይ እንደሆናቸዉ ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/19EIV
Titel “Ethio-Korean War Veterans Memorial in Addis Addis Ababa”. Around 6000 Ethiopian troops served in the Korean War. 122 Ethiopian troops died and 526 were wounded in action. Thema: In 1951, the United Nations formed a coalition to fight against communist North Korean and Chinese forces on the Korean peninsula. The Ethiopian troops (Kagnew Battalion) was comprised of then-Emperor Haile Selassie's personal body guards. During three years in combat, three Kagnew battalions served in Korea. Another arrived following the cease fire. Ethiopian troops fought alongside the U.S. Army's 32nd Infantry Regiment, under the 7th Infantry Division, taking part in hundreds of battles to include action in the Iron Triangle and the fight for Pork Chop Hill. During the war, 122 Ethiopian troops died and 526 were wounded in action. Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 250713 Schlagworte: “Ethio-Korean War Veterans Memorial in Addis Addis Ababa”
ምስል DW/A. Tadesse Hahn

የደቡብ ኮርያ መንግስት፤ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ ለተሰለፉ እና አሁን በህይወት ለሚገኙ ወደ 340 ለሚጠጉ አባት ዘማች ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆን ለዘማች ልጆችና የልጅ ልጆችም ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ የነጻ ትምህርት እድል በመስጠት ላይ ይገኛል። በ21 ዓመታቸዉ ወደ ኮርያ የዘመቱት እና የአሁኑ የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ስለማህበሩ እንዲህ ይገልጻሉ፤ በኮርያዉ ጦርነት ላይ ከዘመቱት መካከል ሻምበል ይልማ በላቸዉ ይገኙበታል፤ ሻንበል በላቸዉ፤ ከኢት ዮጵያ ተነስተን ኮርያ እስክንደርስ ወደ ሃያ ቀናት እንደፈጀባቸዉ ያስታዉሳሉ።

9KR-1950-9-0-A3-2 (1327559) Korea-Krieg / US-Soldat im Häuserkampf in Seoul /Foto 1950 Korea-Krieg 1950-53. (Demokr.Volksrep.Nordkorea gegen Rep. Südkorea und UNO-Truppen). - Kämpfe zur Rückeroberung der südkoreanischen Hauptstadt Seoul, die am 28. Juni 1950 von nordkoreanischen Truppen erobert worden war: US-Marininfanteristen im Häuserkampf. - Foto, um September 1950.
ምስል picture alliance/akg-images

ከጅቡቲ ተነስተን በ22 ቀናችን ቱሳን ደረስን ያሉን ሻንበል ይልማ በላቸዉ ፤ ቱሳን የኮርያ ባህር በር መሆኑን አጫዉተዉናል። የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ በበኩላቸዉ በኮርያ ደርሰን የመጀመርያዉ የኮርያ ገጠመኛችን ይላሉ በማስታወስ፤

በኮርያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከ6ሺህ በላይ ወታደሮችን ማሳተፉዋን የገለጹልን ኮሎኔል መለሰ ተሰማ፤ በኮርያ የበጋ ልብስ እና የክረምት ልብስ መለያየቱን፤ ቀን በቀን የምንበላዉ እንጀራ በኮርያ አለመኖሩን አዉቀናል።

የኮርያዉያን ባህል ከኢትዮጵያዉያኑ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ አግንቸዋለሁ ያሉን ሻምበል ይልማ በላቸዉ ኮርያ ሳለን የእረፍት ግዜአችንን ጃፓን ድረስ እየሄድን እናሳልፍ ነበር ብለዉናል።

የማህበሩ ፕሬዝደንት እንደ ይልማ በላቸዉ ከደቡብ ኮርያ በተገኘዉ የነጻ ትምህርት እድል ባለፈው አመት 60 ተማሪዎች ወደ ኮርያ ሄደዉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ 140 ተማሪዎችን ለመላክ ዝግጅቱን አጠናቀናል ብለዋል ። ከነዚህ መካከል የ 25 ዓመቱ ወጣት ሚኪያስ የኋላእሸት ይገኝበታል። ለአንድ ዓመት የሞያ ስልጠና ወደ ኮርያ ለመሄድ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ የነገረን ወጣት ሚኪያስ የኋላ እሸት በወር ሶስት መቶ ዶላር እየተከፈለዉ ወደ አንድ ዓመት ተኩል ግድም የሞያ ትምህርቱን እንደሚከታተል አጫዉቶናል።

***Achtung: SCHLECHTE Qualität - nicht als Teaser- oder Karusselbild verwenden!*** Titel “Ethio-Korean War Veterans Memorial in Addis Addis Ababa”. Around 6000 Ethiopian troops served in the Korean War. 122 Ethiopian troops died and 526 were wounded in action. Thema: In 1951, the United Nations formed a coalition to fight against communist North Korean and Chinese forces on the Korean peninsula. The Ethiopian troops (Kagnew Battalion) was comprised of then-Emperor Haile Selassie's personal body guards. During three years in combat, three Kagnew battalions served in Korea. Another arrived following the cease fire. Ethiopian troops fought alongside the U.S. Army's 32nd Infantry Regiment, under the 7th Infantry Division, taking part in hundreds of battles to include action in the Iron Triangle and the fight for Pork Chop Hill. During the war, 122 Ethiopian troops died and 526 were wounded in action. *** Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 250713
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በነበረው የኮርያ እርስ በርስ ጦርነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካይነት ወደዚያው ከዘመቱ አገራት መካከል ለኢትዮጵያዉያን ብቻ የመታሰብያ ሐዉልት ቆሞ ይገኛል፤ ያሉን የኮርያዉ ዘማች ኮሎኔል መለሰ፤ ትዝ የሚለኝን የኮርያ ዜማ ላዚምላችሁ ብለዉ አዚመዉልናል፤ ለቅንብሩ መሳካት ቃለ ልልስ የሰጡትን በሙሉ በዶቼ ቬለ ስም እናመሰግናለን።

ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ