1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮት ዲ ቯር ምክር ቤታዊ ምርጫ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 8 2009

ኮት ዲቯር በነገው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። እጎአ በ2011 ዓም ከተካሄደው ምክር ምርጫ ርቆ የነበረው ትልቁ የተቃዋሚው የኮት ዲቯር ሕዝባዊ ግንባር ፣ በምህፃሩ «ኤፍ ፔ ኢ» የተባለው በነገው ምርጫ ይሳተፋል።

https://p.dw.com/p/2UQQe
Elfenbeinküste Wahlen Anhänger der Regierungspartei mit Wahlplakaten in Cocody
ምስል Getty Images/AFP/S. Kambou

 

ለኮት ዲቯር  255 የምክር ቤት መንበሮች እንደ ዘንድሮ ጠንካራ ፉክክር  ተካሂዶ አያውቅም።  1337 ዕጩዎች ናቸው ለውድድር የቀረቡት። በአቢጆ የኮኮዲ ሰፈር ብሔራዊው መዝሙር ካለማቋረጥ ይሰማል። የመገናኛ ሚንስትሯ አፉሲያታ ባምባ ላሚን ጥምሩን መንግሥት በመወከል የምርጫ ዘመቻ አካሂደዋል። በዚሁ ጊዜ ምርጫው የያዘውን ትርጓሜ ለመራጮች ለማስረዳት ሞክረዋል።
« እንደራሴዎቹ ሕዝቡን በብሔራዊው ምክር ቤት ውስጥ የሚወክሉ እና ሕጎችን የሚያወጡ ናቸው። »
ይሁን እንጂ፣ ምርጫውን የተለየ ትርኋሜ የሰጠው የዕጩዎች ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲ የቀድሞው ፕሬዚደንት ሎውሮ ባግቦ የኮት ዲቯር ሕዝባዊ ግንባር ፣ በምህፃሩ «ኤፍ ፔ ኢ» የተባለውፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ  ባሁኑ ምርጫ መሳተፉም ሚና መጫወቱን  በአቢጆ የጀርመናውያኑ ፖለቲካ ጥናት ተቋም ተጠሪ ማርቲን ዮር አስረድተዋል።  እንደሚታወሰው፣ «ኤፍ ፔ ኢ» ከ2010-2011 ዓም የርስበርስ ጦርነት ወዲህ ከተካሄዱት ምርጫዎች በጠቅላላ ራሱን አርቆ ነበር  ። «በዚህም የተነሳ በምክር ቤት የተወከሉት እና አብላጫውን ድምፅ ይዘው የቆዩት ገዢው እና ደጋፊዎቹ ፓርቲዎች ብቻ ነበሩ። ይህ ሁኔታ በነገው ምርጫ ሊቀየር ይችል ይሆናል፣ ሊቀየርም ይገባል። »
ባግቦ ከምርጫ 2010 በኋላ በተከተሉት በርካታ ወራት በተፈ,ጠረው ሁከት እና ግጭት  በስብዕና አንጻር ለተፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ ናቸው በሚል በዘ ሄግ ክስ ተመስርቶባቸዋል ፣ የአስመራጩ ኮሚሽን እና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች አላሳ ዋታራን የፕሬዚደንታዊው ምርጫ አሸናፊ ቢሏቸውም፣ ባግቦ ውጤቱን ለመቀበል ዝግጁ ባልሆኑበት ድርጊት በተከተለው ሁከት  3,000 ገደማ ሲሞቱ፣ ብዙዎች ተፈናቅለዋል። ሀገሪቱ ከዚያን መዘዝ ጋና አላገገመችም። 
ኢሲያካ ሶንጋሬ በአቢጆ የኮኮዲ ሰፈርን በመወከል ለተቃዋሚው የ«ኤፍ ፔ ኢ» ፓርቲ በተወዳዳሪነት  ቀርበዋል። ፓርቲያቸው እንዳዲስ ራሱን አደራጅቶ መቅረብ እንዳለበት ነበር በምርጫው ዘመቻ ወቅት የገለጹት። 
« እኛ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ራሳችንን እንደአዲስ  ለምናዋቅርበት ጉዳይ ነው። »
ይሁንና፣ አንዳንዶቹ የፓርቲ ጓዶቻቸው  የሶንጋሬን አስተሳሰብ አይቀበሉትም። እነዚህ ወገኖች የሚፈልጉት አሁንም ከምክር ቤታዊው ምርጫ መራቅ ነው። ምክንያቱም፣ ይላሉ ማርቲን ዮር፣
«ባንድ በኩል ሎውሮ ባግቦ ከሀገር እጅግ ርቀው ፣ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት ክስ በመሰረተባቸው  ዘ ሄግ ነው የሚገኙት።  ይህም ቢሆን ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ ኑሮ ውስጥ አሁንም ትልቅ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። ይኸው ተፅዕኗቸውም ከተቃዋሚው ወገን መካከል ከፊሉ፣ በተለይም  አክራሪ አቋም የያዘው የ«ኤፍ ፔ ኢ» አንጃ ባግቦ ወደ ሀገር እንዲመለሱ እስከመጠየቅ ርቀው እንዲሄዱ አድርጓል። »
በኮት ዲቯር ፕሬዚደንቱ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ባለፈው ጥቅምት ወር ሕዝበ ውሳኔ በተደረገበትም ጊዜ ቢሆን  እነዚሁ ከፊል የ«ኤፍ ፔ ኢ» አባላት ሕዝቡ በበዚሁ ሬፈረንደም እንዳይሳተፍ ሰፊ ቅስቀሳ ማካሄዳቸው አይዘነጋም።  የሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ በአብላጫው የሀገሪቱ ሕዝብ ዘንድ አካራካሪ ቢሆንም፣  ከመራጩ የኮት ዲቯር ሕዝብ መካካል 40% ብቻ በተሳተፈበት ሕዝበ ውሳኔ ሊፀድቅ ችሏል።  
በነገው ምክር ቤታዊ ምርጫ ላይ በጥቅምቱ ሕዝበ ውሳኔ ከተሳተፈው የሚበልጥ መራጭ ሕዝብ ይሳተፍ ይሆን አይሆን ለመገመት አዳጋች ነው፣ እንደ ማርቲን ዮር አስተያየት።  
ሕዝቡ በፖለቲካው ሂደት በግልጽ የተሰላቸ ነው የሚመስለው። ሕዝቡ፣ አሁንም ለብዙዎች ጥሩ ባልሆነው የኑሮ ሁኔታው እጅግ ትልቅ ቅሬታ አለበት። በ2010 እና 2011 የያየው ዓይነቱ ግጭት እና ሁከት እንደገና እንዳይነሳም ስጋት አድሮበታል። »
ማርቲን ዮር ግን ምርጫው በሰላማዊ መንገድ ይከናወናል የሚል ብሩሕ አመለካከት ነው ያሰሙት። ለምክር ቤታዊው ምርጫ በተወዳዳሪነት ከቀረቡት 1337 ዕጩዎች  መካካ,ል ወደ 200 የሚጠጉ ሴቶች  የእንደራሴነቱን መንበር የማግኘት ተስፋ ሰንቀው  ተንቀሳቅሰዋል።
እስከዛሬ በሀገሪቱ ምክር ቤት ውስጥ የተወከሉት ሴቶች እንደራሴዎች መካከል 25 ብቻ ነበሩ ሴቶች። ከነዚህም በነገው ምርጫም የሚወዳደሩት ያስሚን ኦዌዤኒን አንዷ  ሲሆኑ አንድ ምኞት አላቸው፣ ይኸውም፣
«የምችለውን አድርጌአለሁ። ሴቶች በሁሉም የአመራር ዘርፎች ውስጥ ተጠናክረው እንዲወከሉ እመኛለሁ። »
ይሁን እንጂ፣ ብዙ የኮት ዲቯር ሴቶች ትምህርት ቤት አልሄዱም፣ አስፈላጊውንም ድጋፍ አላገኙም።  
የቀድሞ የምክር ቤት እንደራሴ የነበሩት በርቲ ንድሪ ሴቶች ከወንዶች እኩል በሁሉም የኑሮ ዘርፍ እኩል እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ሙከራ ጀምረዋል።
« ይህ የሚፈለግ ነገር ነው።  ላይቤርያ ሴት ፕሬዚደንት አላት። በጎረቤታችን ሀገር እንደየታየው እኛም  አንድ ቀን ሴት ፕሬዚደንት እንደሚኖረን ተስፋ አለኝ። ይህ ኮት ዲቯርን የሚጠቅም ነው።  በሕይወት እያለሁ ለኮት ዲ ቯር ሴት ፕሬዚደንት ተመርጣ  እንዲሚያሳየኝ ተስፋ አፈደርጋለሁ። ይህን ነው በርግጥ የምመኘው። »

PolitikAfrikaWahlParlamentswahlKampagneElfenbeinküste Wahlen Wahlplakat in Abidjan
ምስል Getty Images/AFP/S. Kambou
Elfenbeinküste Parlament
ምስል Getty Images/AFP/S. Kambou
Elfenbeinküste Wahlen Wahlveranstaltung der RHDP in Cocody
አፉሲያታ ባምባ ላሚንምስል Getty Images/AFP/S. Kambou

ፍሪደሪከ ዩንግ ሚውለር/አርም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ