1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወለኔ ህዝቦች ጥያቄና አቤቱታ

ዓርብ፣ ሰኔ 27 2006

ፓርቲው በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በአባላቱና በአመራር አካላት እንዲሁም በደጋፊዎቹ ላይ የመብት ጥሰት መፈፀሙንና ኢ ህገ መንግሥታዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/1CW21
Karte Äthiopien englisch

የማንነት እውቅና እንዲሰጠው ከዓመታት በፊት የጠየቀው የወለኔ ህዝብ ጥያቄው መልስ ካለማግኘቱም በላይ ለልዩ ልዩ ስቃይ መዳረጉን የወለኔ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምህፃሩ ወህዴፓ ገለፀ ። ፓርቲው በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በአባላቱና በአመራር አካላት እንዲሁም በደጋፊዎቹ ላይ የመብት ጥሰት መፈፀሙንና ኢ ህገ መንግሥታዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አስታውቋል ።ችግር መኖሩን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ ጥያቄው እስኪመለስ ድረስ ህዝቡ ተረጋግቶ በትዕግስት እንዲጠብቅ ለማድረግ እንደሚጥር አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ