1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወሊድ መከላከያ ለወንዶች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 14 2001

ስለወሊድ ቁጥጥር ሲነገር በቀጥታ የሚታሰበን ሴቶች ሊወስዱት የሚገባዉ ቅድመ ወሲብ ጥንቃቄ መሆኑ አያነጋግርም።

https://p.dw.com/p/IudM
ምስል Michael Zitzmann

ወንዶችም በዚህ የጋራ ኃላፊነት እንዲሳተፉ የሚያደርግ ግኝት ብቅ ብሏል። የወንዶች የወሊድ መከላከያ መድሃኒት። ይህ መድሃኒት በተለያየ መልኩ ነዉ የቀረበዉ። በመርፌ፤ ቆዳ ላይ በሚቀባ ክሬምና በሰዉነት ዉስጥ በሚቀበር መልኩ። ምርምሩ ዉጤታማነቱ እስካሁን በ400 ጥንድ ባልና ሚስቶች ላይ ተሞክሯል። እዚህ ጀርመን በሙንስተር ከተማ ብቻም ሃምሳ ጥንዶች ሞክረዉታል። እንደታሰበ ምርምሩ ከዘለቀና የመድሃኒት ፋብሪካዎች ሊያመርቱት አቅሙ ካላቸዉ ቢያንስ በአዉሮፓዉያኑ 2012ዓ,ም ገበያ ላይ ይዉላል ተብሎ ይጠበቃል።

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ