1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልቃይት አቤቱታ

ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2008

የወልቃይት ህዝብ ላነሳዉ የማንነት ጥያቄ በሀገሪቱ ህገ መንግሥት መሠረት ምላሽ ለማግኘት እንደሚንቀሳቀስ የሚገልፀዉ አስተባባሪ ኮሚቴ ህዝቡ ያቀረበዉን ፍትሀዊ ጥያቄ የአካባቢዉ ባለስልጣናት ወደጎን ብለዉ ተፅዕኖ እያደረሱበት እንደሆነ ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/1I0ao
Fasil Schloss Gonder Äthiopien
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

[No title]

የህዝቡን ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ ወደአዲስ አበባ መጓዛቸዉን የሚናገሩት የኮሚቴዉ አባላት ብዙ ተንገላተዉ መግባት ቢችሉም አቤታቸዉን ካቀረቡ በኋላ አሸባሪዎች ተብለዉ ተይዘዉ ለሰዓታት መመርመራቸዉንም ይናገራሉ።

ቀደም ሲል የወልቃይትን ህዝብ የአማራነት ጥያቄ ያነሱ ሰዎችም እስካሁን ያሉበት እንኳ አይታወቅም ይላሉ የአስተባባሪ ኮሚቴዉ አባላት። ከሁለት ሺህ ሰባት ወዲህም ሀገሪቱ ከራሷ አልፎ ለአፍሪቃ የሚበቃ ህገ መንግሥት እያላት የእኛ ጥያቄ በህገ መንግሥቱ ምላሽ ያገኛል በሚል ምሁራንንና ሀገሬዉን በማማከር ለህዋሃት ጽህፈት ቤት፤ ለአማራ ክልል፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጨምሮ ለሚመለከተዉ ሁሉ በሰነድ የተደገፈ አቤቱታቸዉን እንዳቀረቡም አስረድተዋል።

Karte von Äthiopien
ምስል AP GraphicsBank/DW

የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላቱ እንደሚሉት አሁንም ይህን ጥያቄ ያነሳሉ ያስተባብራሉ ተብለዉ የሚጠረጠሩ ሰዎች በአካባቢዉ ለወከባ ተዳርገዋል። ድብደባ የተፈጸመባቸዉ ግለሰብም ጎንደር ሃኪም ቤት እንደገቡም ጠቅሰዋል። መረጃዎቹን ለማጣራት ወደወልቃይት ዞን ባለስልጣናት ስልክ ብንደዉልም ስብሰባ ላይ ነን እና ሥራ ላይ ነን በሚሉ ምክንያቶች ለጥያቄያችን ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። የሀገሪቱ የፌደራል ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ደረሰብን ስላሉት የእስር እንግልት እሳቸዉም ሆነ መሥሪያ ቤታቸዉ የሚያዉቀዉ ነገር የለም ካሉ በኋላ ያቀረቡት ጥያቄ ግን በሽምግልና እየታየ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ