1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2008

የወሳኝ ኩነቶች ማለትም የልደት የሞት የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባዎች ከነገ ሐምሌ 30 ፣2008 ዓም ጀምሮ በይፋ ይጀመራል ።

https://p.dw.com/p/1Jbkt
Geburtsurkunde, Äthiopien
ምስል Getachew Tedla HG

[No title]

በኢትዮጵያ ወሳኝ ኩነቶች እንደተከሰቱ ህብረተሰቡ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲያስመዘግብ ጥሬ ቀረበ ። ዛሬ በአዲስ አበባ በሂልተን ሆቴል በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባሰሙት ንግግር የወሳኝ ኩነቶች ማለትም የልደት የሞት የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባዎች ከነገ ሐምሌ 30 ፣2008 ዓም ጀምሮ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀው ህብረተሰቡም ኩነቶቹን በማስመዝገብ የበኩሉን ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ።በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ከፕሬዝዳንቱ ሌላ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተጠሪዎችም ተገኝተዋል ። ስነስርዓቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ