የወታደሩን ታማኝነት አጠያያቂ ያደረገዉ ክስተት?

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:56 ደቂቃ
11.10.2018

የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ነገሩን ይባስ አጠያያቄ አድርጎት ነበር

ቤተ-መንግሥት አካባቢ በርካታ ወታደሮችና ጦር መሣርያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መታየታቸዉ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ስጋት እና ከፍተኛ ውጥረት ቢፈጥርም ማምሻዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቴሌቭዝን መስኮት ቀርበዉ ሰላም መሆኑን ከመግለፃቸው በመጠኑ እፎይታ አሳድሯል።  

ረቡዕ መስከረም መስከረም 30 እለት ቤተ-መንግሥት አካባቢ በርካታ ወታደሮችና ጦር መሣርያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መታየታቸዉ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ስጋት እና ከፍተኛ ውጥረት ቢፈጥርም ማምሻዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቴሌቭዝን መስኮት ቀርበዉ ሰላም መሆኑን ከመግለፃቸው በመጠኑ እፎይታ አሳድሯል። ውጥረት በታየባት አዲስ አበባ ከረፋድ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ነገሩን ይባስ አጠያያቄ አድርጎት ነበር ያረፈደዉ።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባና አካባቢዋ በተለያዩ ግዳጆች ላይ መቆየታቸውን የገለጿቸው የሠራዊቱ አባላት ጋር ተገናኝተው ስለሚያሳስቧቸው ጉዳዮች መወያየታቸውን ተናግረዋል። ይሁንና «ከ200 የሚበልጡት ወታደሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደሞዝዛቸዉን እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን እንዲያስተካክሉላቸዉ ለመጠየቅ ነዉ ወደ ቤተ-መንግሥት የመጡት» መባሉ ሌሎች ጥያቄዎች ን አጭሮአል።  የወታደሮቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ቤተ መንግሥት መሄዳቸዉም የተለያዩ አንድምታዎችን አያሰናዘረ ነዉ። በዚሁ ጉዳይ ላይ አዜብ ታደሰ የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ሃሌሉያ ሉሌን አነጋግራቸዉ ነበር። 


አዜብ ታደሰ  
አርያም ተክሌ

ተከታተሉን