1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወይዘሮ ሙፈሪያት ማስጠንቀቂያ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 14 2011

ወይዘሮ ሙፈሪያት በፓርቲያቸዉ ጉባኤ ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት አንዳድ የደኢሕዴን ባለስልጣናት ከፓርቲዉ ዉጪ ያሉ «አለቆቻቸዉ» ላላሏቸዉ ወገኖች አጎብዳጆች ናቸዉ

https://p.dw.com/p/3ODrs
Logo von SEPDM

ደኢሕዴንን የሚያዉኩ «ጥርግ ማለት ይችላሉ» ሙፈሪያት

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀመንበር ሙፈርያት ካሚል የፓርቲያቸዉን ባለስልጣናት «በሁለት ቢላ የሚበሉ፣ አድሐሪ» በማለት ወቀሱ። ከደቡብ ኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበርነት በተጨማሪ የፌደራሉን የሰላም ሚንስትርነት ስልጣን ደርበዉ የያዙት ወይዘሮ ሙፈሪያት በፓርቲያቸዉ ጉባኤ ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት አንዳድ የደኢሕዴን ባለስልጣናት ከፓርቲዉ ዉጪ ያሉ «አለቆቻቸዉ» ላላሏቸዉ ወገኖች አጎብዳጆች ናቸዉ። የሲዳማን ጨምሮ በተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያ ዞኖች የሚኖሩ የተለያዩ ጎሳ ፖለቲከኞች የክልልነት አስተዳደር በይፋ መጠየቅ ከጀመሩ ወዲሕ ደኢሕዴን ክፉኛ ተዳክሟል ነዉ የሚባለዉ። ወይዘሮ ሙፈሪያት እንደሚሉት የፓርቲዉን ሥራና አሰራር የሚያዉኩ ባለስልጣናት «ጥርግ» ማለት ይችላሉ።«ግን» አሉ ሊቀመንበሯ  በቅድሚያ የኃላፊነትን ሒሳብ አወራርዶ ነዉ ታዲያ።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ