1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣቶች መድረክ

እሑድ፣ ጥቅምት 22 2002

ይነጋል ይመሻል፤ ዛሬ ወደ ትናንትነት ይቀየራል። ደግሞ ሌላ ነገ ይመጣል። ትናንት ሊሆን ማለት ነው። ዑደቱ ሳይዛነፍ ለዘመናት ይቀጥላል። ለመሆኑ ስንቶቻችን እንሆን ፈፅሞ የማይመለስ ጊዜያችንን በአግባቡ የምንጠቃም?

https://p.dw.com/p/KKSB
ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም
ጊዜ ቆሞ አይጠብቅምምስል BilderBox

መዓልትና ሌሊት እየተቀባበሉ ቀናትን ሲወልዱ ብዙም ትኩረት ላንሰጠው እንችል ይሆናል። ሆኖም በትናንት እና በዛሬ ቅብብሎሽ መካከል እንደዋዛ ወጣትነት ዘመኔን ጨርሻለሁና አሰናብቱኝ የሚልበት ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀርም። ታዲያ የወጣትነት ጊዜያቸውን በአግባቡ የተጠቀሙ ሲደሰቱ፤ የጊዜ ዑደቱን ሳያስተውሉ ጊዜ ያለፈባቸው ደግሞ ለፀፀት መዳረጋቸው የማይቀር ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ