1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉኃ አቅርቦት እጥረት ችግር በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bula
ዓርብ፣ ጥር 5 2009

ኢትዮጵያ  ከ12 የወንዝ ሸለቆች በየዓመቱ 122 ብሊዮን ሜትር ኪውብ መጠን ውኃ፣ እንዲሁም ከ2,6-6,5 ቢሊዮን ሜትር ክዩብ የመሬት ዉስጥ የዉኃ አቅም እንዳላት የአለማቀፉ የዉኃ ማኔጀመንት ተቋም ጥናት ያመለክታል።  

https://p.dw.com/p/2VieU
Äthiopien Flüchtlingslager Flüchtlinge aus Eritrea
ምስል Reuters/T. Negeri

Water Shortage in Ethiopia - MP3-Stereo

ይሁን እንጂ፣ በአገሪቱ የመጠጥ ዉኃ አቅርቦት እጥረት ለማኅበረሰቡ ትልቅ ማነቆ ሆኖ ቀጥለዋል። አሁንም በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች፣ ማለትም በመቀለ፣ በጎንደር፣ በሃረሪ እንዲሁም በሶማሌና በአፋር ክልሎች  ከፍተኛ የመጠት ዉኃ አቅርቦት እጥረት እንዳለ ከነዋሪዎች ለመረዳት ተችለዋል። ለዚሁ ችግር የዉኃ ኃብትን ካለማልማት እና ከዚሁ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ጉዳዮች ምክንያት መሆናቸዉን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮግራፊ ባለሙያ ዶክተር ሙሉንሄ ወልደፃድቅ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ይህ የዉኃ እጥረትም የአገሪቱ ወና ከተማና ለብዙ ተቋሞች መድና የሆነችዉን አድስ አበባም በክፉኛ ኢያጠቃ መሆኑን ዶክተር ሙሉኔ ይናገራሉ። ለዝህም ችግር መንሴ የምሆነዉ የዉኃ ሃብት እጥረት ሳይሆን የፊላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ነዉም ይላሉ። የከርሰ ምድር ዉኃን አዉጥቶ ለመጠቀምም ሆነ ወራጅ ዉኃን ቀልብሶ ለመጠጥ ዉኃ ለመጠቀምም ብሆን የቴክኖሎጅ፣ የሰዉ ኃይልና የካፒታል አቅም ያስፈልጋል ያሉት ዶክተር ሙሉነህ ሌሎች ተግዳራቶችንም ዘርዝረዋል።

የመንግስት ተቋማትን ሳይጨምር ከ40 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሃገሪቱ የዉኃ አቅርቦት ላይ እንደሚሰሩ ዘገባዎች ይጦቁማሉ። ከነዚህም ዋተር ኤድ/WaterAid/ የተሰኘዉ አንዱ ስሆን በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ ትግራይና በደቡብ ክልሎች በዋተር ኤድ የዉኃና ንፅህና አጠባበቅ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ቭንሴንት ኬስ ለዶቼቬሌ ይናገራሉ። ቭንሴንት ኬሲ መሬት ላይ ስላለዉ ያለዉን ችግር እንዲህ ይናገራሉ፣ «ለዚህ ችግር መንስዔ አንዱ የአቅም ጉዳይ ነዉ። አቅም ስንል የምፈለገዉን አገልግሎት በምፈለገዉን ፍጥነት የማቅረብ ጉዳይ ነዉ። አካባቢዉ የልማት ቦታ ስለሆነ  የተፈጠረዉን እጥረት ለመሸፈን በጣም ከባድ ነዉ። ከባዱ ነገር ሁሉም ሰዎች አገልግሎት የማግኘት እድል የላቸዉም። በተጨማርም ወደ እነሱ አገልግሎትን ለመዉሰድ ምክንያቶችና የምንፈለገዉ ፍጥነት ከባድ ነዉ። ይህም ግዜ ይወስዳል። እርግጠኛ ነን አሁን ባለን ኃይል ከቀጠለን የተሻለ ማሻሽዮች ይኖራሉ።»

የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር መጨመሩና የኢኮኖም እድገት ምጣኔ  አለመጣጣሙ ለሚከሰተዉ የመጠጥ ዉኃ እጥረት አንዱ መሰረት ነዉ ሲሉ ዶክተር ሙሉነህ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ