1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

ሐሙስ፣ ጥር 12 2014

ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች አንደነገሩት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ጉባኤዉ አዲስ አበባ ዉስጥ እንዳይደረግ ግፊት ሲደረግ ነበር።ዛሬ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እዚያዉ አዲስ አበባ ዉስጥ ስለሚነጋገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶች ተልዕኮ ግን አምባሳደር ዲና መረጃ የላቸዉም

https://p.dw.com/p/45qf6
Äthiopien Hawassa | Ambassador Dina Mufti
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

35ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአካል አዲስ አበባ ዉስጥ እንዳይካሔድ የተደረገዉን ግፊት የኢትዮጵያ መንግስት ማክሸፉን የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።ሚንስቴሩ ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች አንደነገሩት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ጉባኤዉ አዲስ አበባ ዉስጥ እንዳይደረግ ግፊት ሲደረግ ነበር።ዛሬ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እዚያዉ አዲስ አበባ ዉስጥ ስለሚነጋገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶች ተልዕኮ ግን አምባሳደር ዲና መረጃ የላቸዉም።ቃል አቀባዩ ስለሕዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ትግራይ ዉስጥ ያደርሰዋል ስለተባለዉ የአየር ድብደባና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ