1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2004

የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ ከዕጅ ወደ አፍ ኑሮን ለሚገፋት ለብዙሃኑ የአገሪቱ ዜጎች ብርቱ ፈተና ሆኖ መኖሩን የማያውቅ ማንም የለም።

https://p.dw.com/p/15Ux8
መርካቶ ገበያምስል picture alliance/kpa

የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ ከዕጅ ወደ አፍ ኑሮን ለሚገፋት ለብዙሃኑ የአገሪቱ ዜጎች ብርቱ ፈተና ሆኖ መኖሩን የማያውቅ ማንም የለም። የዋጋው ግሽበት ከአሥር በመቶ ያላነሰ የኤኮኖሚ ዕድገት ታየባቸው በሚባሉት ባለፉት ዓመታት ውስጥም እየጨመረ ሲሄድ ቆይቷል። ይሁንና የአገሪቱ ማዕከላዊ ስታቲስቲክ ቢሮ ትናንት ባቀረበው ወርሃዊ መገልጫው እንደጠቀሰው ግሽበቱ በተለይም በምግብ ምርቶች ዋጋ ንረት ጋብ ማለት የተነሣ ባለፈው ግንቦት ከነበረበት 25,5 በመቶ በተከታዩ ሰኔ ወር ወደ 20,9 ከመቶ ዝቅ ብሏል። ግሽበቱ በተከታታይ ለአራተኛ ወር ሲቀንስ በተጠቀሰው ጊዜ የምግብ ዋጋ ግሽበት ከ 29,2 ወደ 21,5 ከመቶ ማቆልቆሉም ነው። በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት በጥቂቱ መጨመሩ ተመልክቷል። ለመሆኑ የምግብ ዋጋ ግሽበት በ 8 ከመቶ መጠን ለመቀነሱ እንዲህ ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ምን መረጃ ምክንያቶች አሉ፤ በገበዮች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶችስ ይታያሉ ወይ? ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ