1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውህደት ትምሕርት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ኅዳር 14 2003

« እነዚህ ደንቦች በርግጥ ለመረዳት ቀላል ናቸው ። እዚህ መኖር የሚፈልግ ጀርመንኛ መማር አለበት ። እዚህ የሚኖር ሰው ህጎቻችንንና እሴቶቻችንን ማክበር ይገባዋል ። ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በኛ ዘንድ ተቀባይነት አለው ። ይህን ማድረግ የማይፈልግ ማዕቀብ ይጠብቀዋል ። ያን ያህል ቀላል ነው ። »

https://p.dw.com/p/QGIo
ምስል dpa
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በተካሄደው የክርስቲያን ዲሞክራቶች ህብረት ፓርቲ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የውጭ ዜጎች ከጀርመን ህብረተሰብ ጋር ተዋህደው ለመኖር የሀገሪቱን ቋንቋው ማወቅ ህጉንና ባህሉንም ማክበር እንደሚገባቸው የሰጡት ማሳሰቢያ ነው ። በዛሬው ዝግጅታችን ጀርመን ለሚኖሩ የውጭ ዜጎች ከሚሰጠው የውህደት ትምህርት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ነው የምናነሳው ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ