1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውስጥ አካላትን አጎልቶ የሚያሳየው ግዙፍና የረቀቀ መሣሪያ፣

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001

በጀርመን ሀገር የምርምር ማዕከል በሆነችው በአንዳንድ ረገድም ፣ በአውሮፓ የመሪነቱን ሥፍራ በያዘችው ከተማ ፣ በዩሊኽ፣

https://p.dw.com/p/HpQn
በዩሊኽ፣ የህክምና ሥነ ቴክኒክ ያስገኘው ግዙፉና የረቀቀው መሣሪያ፣ምስል Forschungszentrum Jülich

በአውሮፓ ወደር እንደሌለው ከተነገረለት ግዙፍ ኮምፒዩተር ሌላ፣ ለህክምና ሥነ-ቴክኒክ እጅግ ጠቃሚ የሆነ፣የሰውነት የውስጥ አካላትን ም ሆነ ኅዋሳትን እጅግ አጉልቶ በማሳየት ይበል ያሰኘ ግዙፍና ረቂቅ መሣሪያ ተሠርቷል። 1,500 እስኩየር ሜትር ስፋት ባለው ቦታ በተሠራ ህንጻ ውስጥ የሚገኘው በመግነጢሳዊ ኃይል የሚሠራው መሣሪያ ፣«ቶሞግራፍ»፣ 4 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ የማግኔቱ ክብደት 57 ቶን ነው። እንደ ምድራችን የተፈጥሮ መግነጢሳዊ ኃይል፣ 190,000 እጥፍ ጉልበትም ያለው ነው።

ተክሌ የኋላ/አርያም ተክሌ