1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ሙያተኞች ፍለጋ በጀርመን

ማክሰኞ፣ ኅዳር 18 2005

በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ የውጭ ዜጎችን ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ለመሳብ ሥራ ላይ የዋለው አሰራር በተለይ በጀርመን የተጠበቀውን ያህል ማራኪ የሆነ አይመስልም ። ምክንያቱ ምን ይሆን ? ጀርመንስ የውጭ ዜጎች በብዛት መሳብ ከቻሉ ሃገራት ምን ትማራለች የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

https://p.dw.com/p/16qp4
Logo Blue Card
ARCHIV - Ein frisch operierter Patient wird am Mittwoch (09.09.2009) auf der Intensivstation in der Universitätsklinik Köln behandelt. Nordrhein-Westfalen steht vor einem drastischen Arbeitskräftemangel: Ohne ein entschiedenes Gegensteuern verliert das bevölkerungsreichste Bundesland bis 2025 rund 1,3 Millionen Erwerbspersonen, darunter etwa eine Million Fachkräfte, wie die Regionaldirektion NRW der Bundesagentur für Arbeit am Mittwoch (12.10.2011) mitteilte. Schon jetzt fehlen in einigen Branchen Facharbeiter. Besonders gelte das für Krankenschwestern, Altenpflegekräfte, Erzieher, Köche, Elektroniker, Dachdecker und Fliesenleger, die teilweise schon NRW-weit händeringend gesucht werden. Foto: Oliver Berg dpa/lnw +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa
Symbolbild Blue Card Europa Konkurrenz zur Greencard der USA
ምስል chromorange

በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ የውጭ ዜጎች በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሥራትና መኖር የሚያስችላቸው የተለየ የሥራና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጣቸው በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የፀደቀው እጎአ በ2009 አ.ም ነበር ። ከአውሮፓ ህብረት ባንዲራ ቀለም ሰማያዊ ተወስዶ «ብሉ ካርድ» ወይም ሰማያዊ ካርድ ተብሎ የሚጠራው ይሽው የስራና የመኖሪያ ፈቃድ በተወሰነ ደረጃ ከአሜሪካኑ ግሪን ካርድ ጋር ይቀራረባል ። የብሉ ካርድ እቅድ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው በ 2007 አ.ም በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆሴ ማኑዌል ባሮሶ ነበር ። ባሮሶ በወቅቱ እንዳስረዱት ብሉ ካርድ ያስፈለገው በአውሮፓ ህብረት ወደፊት በሚያጋጥመው በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ፣ የውጭ ዜጎችም በህብረቱ አባል ሃገራት በሥራ ምክንያት ሲዘዋወሩ በሚያጋጥማቸው ችግር ፣ የ27 ቱ የህብረቱ አባል ሃገራት የውጭ ዜጎችን የሚቀበሉባቸው አሰራሮች በመለያየታቸው ምክንያት ነው ። የብሉ ካርድን እቅድ ዴንማርክ አይርላንድና ብሪታኒያ ከመጀመሪያውም አልተቀበሉም ። አባል ሃገራት ብሉ ካርድን እጎአ ከሰኔ 2011 በፊት ሥራ ላይ እንዲያውሉት ቢደነገግም ኦስትሪያ ቆጵሮስና ግሪክ አሰራሩን ተግባራዊ አላደረጉም ። ጀርመንም ካለፈው አመት ነሐሴ አንስቶ ነው በከፈተኛ ደረጃ ለሰለጠኑ የውጭ ዜጎች ብሉ ካርድ መስጠት የጀመረችው ። ይሁንና ብሉ ካርድ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተጠበቀውን ያህል እጅግ የሚፈለጉ ከፍተኛ ሥልጠና የወሰዱ የውጭ ዜጎች እንዳልተገኙ ነው የሚነገረው ። ባለፉት 3 ወራት ብዙ የውጭ ዜጎች ጀርመን ውስጥ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን ሲሻሙ አልታየም ። ይህም ከወዲሁ ብዙ ጥያቄዎችን ማስነሳት ጀምሯል ። ብሉ ካርድ የታለመለትን ግብ ሊመታ አልቻለም ማለት ነው ? ችግሩ ምንድነው ? የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች እየተነሱ ነው ። ከጀርመን የኢንዱስትሪና የንግድ ምክር ቤት ምክር ቤቶች ማህበራት ሽቴፋን ሃርዴገ ከአሁኑ ብሉ ካርድ ግቡን አልመታም ብሎ መደምደም እንደማይቻል ነው የሚናገሩት ። በርሳቸው አስተያየት አሁን አዲሱን የሥራ ና የመኖሪያ ፈቃድ ይበልጥ ማስተዋወቅ ያሻል ።
« ባላፉት ጊዜያት የሰለጠኑ ባለሞያዎች ጀርመን ውስጥ ነብተው መሥራት ቀላል አልነበረም ። አሁን ግን በመሰረቱ ቀላል ሆኗል ። እርግጥ ነው በውጭ ያሉት የሚፈለጉ ባለሞያዎችም ይህን ማወቅ አለባቸው ። ለዚህም ተጨማሪ መረጃዎችን መስጠትና ሃገሪቱንም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ። »
ብሉ ወይም ሰማያዊ ካርድ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ከሆኑ ሃገራት ለሚመጡና ቢያንስ 44 ሺህ 800 ዩሮ የሚደርስ አመታዊ ደሞዝ የሚያስገኙ ሥራዎች ላገኙ በከፍተኛ ደረጃ ሥልጠና ለወሰዱ ሰዎች የሚሰጥ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ነው ። ካርዱ መጀመሪያ ለ 3 አመት ነው የሚሰጠው ። ከዚያም ፈቃዱ በየጊዜው ይታደሳል ። ሰማያዊ ካርድ ማግኘት የቻለ የውጭ ዜጋ ቤተሰቡን ሥራ ዋዳገኘበት የአውሮፓ ሃገር ይዞ መምጣት ይችላል ፤ በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራትም እንደ ልብ የመዘዋውር ፈቃድም አለው ። ያም ሆኖ ብሉ ካርድ በጀርመን የውጭ ዜጎችን ለጊዜውም ቢሆን በብዛት ያልሳበበት ምክንያት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ጀርመን ለብዙ አሥርት አመታት ካናዳንና አሜሪካንን እንደመሳሰሉ ሃገራት የውጭ ዜጎችን በመቀበል የምትታወቅ ሃገር አለመሆኗ ነው ።
እናም በነርሱ አስተያየት ይህ የሃገሪቱ ገፅታ ህግን በመለወጥ ብቻ በአንዴ ሊለወጥ አይቻልም ፤ ከህጉ ጎን ለጎን ፣ ብሉ ወይንም ሰማያዊ ካርድን በውጭ በሰፊው ማስተዋወቅ ይገባል ። በውጭ በሚገኙ የጀርመን ኤምባሲዎች ከፍተኛ ሥልጠና የወሰዱ ባለሞያዎችን የሚያማክሩ የኢሚግሪሽን ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉም ይናገራሉ ። ሽቴፋን ሃርድገ እንደሚሉት የጀርመን ኢንዱስትሪዎች ለበርካታ አመታት በተለይም በአውቶሞቢልና በምህንድስና ዘርፍ ፣ በጥናትና ምርምር መስክ የባለሞያዎች እጥረት አለ ። በጀርመን ነርሶችም በእጅጉ ይፈለጋሉ ።
« በእነዚህ የስራ ዘርፎች ነው የበርካታ ባለሞያዎች እጥረት ያለው ። እናም በጣም የሚገርመው መሐንዲሶችና ምሁራን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በተግባረ እድ ሞያ የሰለጠኑ ሰዎች እጥረት ማጋጠሙን ኢንዲስትሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገነዘቡት ሄደዋል ። እናም ተስማሚ የሆኑ ለሥራው የሚፈለጉ ሠራተኞችን ማግኘት አዳጋች እየሆነ መጥቷል »
የጀርመን የሠራተኞች ጉዳይ አጥኚ ተቋም እንዳስታወቀው እጎአ በ2020 ጀርመን 240 ሺህ የሚሆኑ መሐንዲሶች እጥረት ያጋጥማታል የኮሎኙ የምጣኔ ሃብት ጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ ክሪስቶፍ ሜትስለር ብሉ ካርድ የውጭ ዜጎች ጀርመን ውስጥ ለመሥራት እንዲያመለክቱ ግልፅ ና በጎ ምልክት ነው ። ሆኖም ተፈላጊውን የሰው ኃይል ለማግኘት ብሉ ካርዱን የማስተዋወቅ ዘመቻ ማካሄድ ያስፈልጋል ። በርካታ የጀርመን ኩባንያዎች የውጭ ሠራተኞችን ለመቀበል ቃል መግባታቸውን ያስታወሱት ሜትስለር የጀርመን ፊደራል መንግሥት ም ሆነ ፌደራዊ ክፍለ ግዛቶች በዚህ ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆኑን ጠቁመዋል


« 1250 የጀርመን ኩባንያዎች ከተለያየ አካባቢ የሚመጡ የውጭ ዜጎችን ለመቀበል ቃል ገብተዋል ። የጀርመን ፌደራል መንግሥትና ፌደራዊ ክፍለ ግዛቶችም እንዲሁ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል ። Make it in Germay « ጀርመንን ምርጫዎ ያድርጉ» የሚለው መሪ ቃል አስደናቂ ነው ። በዚህ ማስታወቂያ አንድ ወጣት ህንዳዊ መሐንዲስ፣ ጀርመን እንዴት መኖር እንደሚቻል ጀርመን ምን ጠብቆ እንደመጣ መረጃ ያስተላልፋል ። ወዲያውኑ የአለም ካርታ በመመልከት ምን አይነት የተግባር እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ህንድ ውስጥ ምን ማግኘት እንደሚችል ለምሳሌ ያህል ከጎቴ የባህል ተቋም ስለ ጀርመን የመጀመሪያውን መረጃ ማግኘት እንደሚቻል ያስረዳል ። »
ጀርመን ውስጥ የሚኖሩ በየሃገራቸው በተለያዩ የሙያ መስኮች ከከፈተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ የውጭ ዜጎች በሰለጠኑበት ሞያ ሥራ ማግኘቱ እስካሁን እንዲህ ቀላል አይደለም ። ብዙውን ጊዜ የትምህርት ማስረጃዎቻቸው እውቅና አይሰጣቸውም ። የተማሩትን ሞያም መለማመድ አይችሉም ። የጀርመን ፌደራል መንግሥት ለእነዚህን ባለሞያዎች ጉዳይ መላ መፈለጉ በጣም ጠቃሚ መሆኑን ሜትስለር ያሳስባሉ ።
« bq portal በመባል የሚታወቅ የመረጃ ማዕከል አለ ። ኩባንያዎችና የንግድ ምክር ቤቶች ከዚህ የመረጃ ማዕከል የሌሎች አገራት የትምህርት ሥርዓት እንዴት እንደሆነ ሊመለከቱ ይችላሉ ። ይሄ በርግጥ ወደኛ የሚመጡትን ሰዎች ብቻ ሳይሆን በዚህ አገር የሚኖሩትንና በጠቅላላው በችሎታቸውም ሆነ በእውቀታቸው የሚቻላቸውንው ሁሉ እያደረጉ የሚኖሩትን የሚያግዝ ነው ። »
እነዚህን ከመሳሰሉ ችግሮች በመነሳት ጀርመን የውጭ ዜጎች በብዛት መሳብ ከቻሉ ሃገሮች ልምድ መውሰድ እንደሚገባት የመስኩ ባለሞያዎች ያሳስባሉ ። ለምሳሌ ጀርመን ካናዳን ከመሳሰሉ በየአመቱ ብዙ የተማሩ የውጭ ዜጎችን መማረክ ከቻሉ ሃገራት ብዙ መማር ትችላለች ። ወደ ካናዳ የሚገባው የውጭ ዜጋ የህዝቧ ቁጥር በየአመቱ በአንድ በመቶ ያሳድገዋል ። ሃገሪቱ የውጭ ዜጎችን የተመለከቱ ፖሊሲዎቿን በየጊዜው ከኢኮኖሚ ፍላጎቷ ጋር እንዲጣጣም በማድረግ ትቀይራለች ። በዚህ ረገድ ጀርመን በውጭ ዜጎች ተመራጭ ሃገር እንድትሆን ራሷን ማራኪ አድራጋ ማቅረብ እንዳለባት ነው የበርሊኑ የስነ ህዝብ ና ልማት ጥናት ተቋም ጥናት ያመለከተው ። የተቋሙ ሃላፊ ራይነር ክሊንግሆልዝ 10 15 አመታት ውስጥ እንሚያጋጥም የሚያሰጋውን የሠራተኛ ኃይል እጥረት ከአወሮፓ ህብረት አባላት ብቻ ማግኘት እንደማይቻል ያስረዳሉ በርሳቸው አስተያየት ፖለቲከኞች የውጭ
ዜጎች ለሃገሪቱ ምን ያህል አስፈላጊና ጠቃሚ እንደሆኑ ህዝቡን ማስገንዘብ ይኖርባቸዋል ። ከዚሁ ጋርም ሃገሪቱን ይበልጥ ማስተዋውቅ ይገባል እንደ ክሊንግ ሆልዝ ።
«ያ ማለት ራሳችንን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ አለብን ። በውጭ ሃገራት ራሳችንን በትጋት ማስተዋወቅ ይኖርብናል ። »

ካናዳ እጎአ ከ 1967 አንስቶ የውጭ ዜጎችን ወደ ሃገርዋ የምታስገባበት ደንብ በተለይ ለቋንቋ ችሎታና ለትምሕርት ደረጃ ትልቅ ቦታ ይሰጣል ። ቋንቋና የትምህርት ደረጃ ከመመዘኛዎቹ 2/3 ሶስተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ ። በካናዳ የሥራ ልምድ ና እድሜም እንዲሁ የተወሰነ ድርሻ ይኖራቸዋል ። ካናዳ የውጭ ዜጎችን የምትቀበልባቸው ሌሎችም መስፈርቶች አሏት ። አንደኛው የቋንቋ ችሎታና የትምህርት ደረጃን የሥራ ልምድንና የመሳሰሉትን መስፈርቶች የሚከተለው ደንብ ነው ። ክሊንግ ሆልትስ እንደሚሉት በካናዳ ተፈላጊዎቹ ከፍተኛ ሥልጠና የወሰዱ የውጭ ዜጎች ብቻ አይደሉም ።
« በተጨማሪ ካናዳ በርግጥ በከፈተኛ ደረጃ የሰለጠኑ የውጭ ዜጎችን ብቻ ሳይሆን በተለይ በጤና አገልግሎቱ መስክ የሚፈልጉ መደበኛ ሥልጠና የወሰዱ ነርሶችን በነዳጅ ዘይት ኢንዱስትሪና በደን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ሠራተኞችንም ጭምር ነው ወደ ሃገርዋ የምታስገባው ። በተለያዩ አካባቢዎች ከክፍለ ሃገሮች ለውጭ ዜጎች ሥራ ለመስጠት የወጡ ልዩ መርሃ ግብሮች አሉ ።»
የውጭ ዜጎች ወደ ካናዳ የሚገቡት የተጨበ ሥራ አግኝተው አይደለም ። ይህ ግን እንደ ክሊንግ ሆልዝ ጎጂ አይደለም ። የውጭ ዜጎች ካሉበት ሳይነሱ ነው ካናዳን ለማወቅ ዝግጅት የሚጀምሩት ። ሃገራቸው ሆነው ስለ ካናዳ ታሪክ ባህልና የአኗኗር ሁኔታ መረጃ የሚሰጡ ትምህርቶች ይወስዳሉ ። እነዚህ ሥልጠናዎችም ለውጭ ዜጎች ኑሮን በካናዳ ቀላል ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል ። በካናዳ ከሃገሬው ነዋሬ የተማረው የውጭ ዜጋ ቁጥር ይበልጣል ። በጀርመን ቢሆን የዪኒቨርስቲ ዲግሪ ያላቸው የውጭ ዜጎች ቁጥር በቅርብ አመታት አድጓል ። በክሊንግሆልትስ እምነት ጀርመን ከካናዳ ልትቀስም የምትችላቸው በርካታ ልምዶች አሉ ።

Dresden (Sachsen): Jindam Shrikant aus Indien arbeitet als Drucker im Tubenwerk Essel in Dresden Klotzsche. Die Essel Deutschland GmbH begann im April des Jahres als deutsch-indisches Joint-Venture. Im Werk, das mit knapp 20 Millionen Mark im neuen Technopark Nord an der Königsbrücker Straße entstand, werden Tuben hauptsächlich für die Dental- und Kosmetik-Industrie produziert. Aus bedruckten Laminatbändern entstehen die Tuben, an einer Anlage bis zu 180 Stück pro Minute. Drucker Jindam Shrikant kam mit einer Green-Card vom indischen Mutter-Unternehmen, denn trotzt hoher Arbeitslosigkeit in Dresden sei es schwer, geeignetes Personal zu finden, so die Geschäftsführung. (DRE478-031100)
ምስል picture-alliance/dpa

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ