1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ዜጎች ጥላቻን ለመታገል የተመሠረተው ህብረት

ዓርብ፣ የካቲት 4 2008

የውጭ ዜጎች ጀርመን መግባታቸውን የሚቃወሙትን የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች እንቅስቃሴና የሚያራምዱትን አመለካከት ለመታገል ያለመ ማህበር ትናንት በርሊን ውስጥ ተመስርቷል።

https://p.dw.com/p/1HuWk
Deutschland Allianz für Weltoffenheit Solidarität Demokratie und Rechtsstaat
ምስል imago/epd/J. Blume

[No title]

በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች ከሃገራቸው የተፈናቀሉ በርካታ የውጭ ዜጎች ጀርመን ውስጥ ይገኛሉ ። በጎርጎሮሳውያኑ 2015 ዓመት ብቻ ጀርመን የገባው ስደተኛ ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ይገመታል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በተባለ ሁኔታ ስደተኞች በብዛት ጀርመን መግባታቸው እዚህ ማነጋገሩ እንደቀጠለ ነው። ከጦርነት ሸሽተው የመጡ ስደተኞችን ጀርመን ወደ ሃገርዋ ማስገባትዋን የሚቀበሉ እንዳሉ ሁሉ እርምጃውን በመቃወም የውጭ ዜጎች ጥላቻን የሚያስፋፉ የህብረተሰብ ክፍሎችም አልጠፉም። የውጭ ዜጎች ጀርመን መግባታቸውን የሚቃወሙትን

የህብረተሰብ ክፍሎች እንቅስቃሴና የሚያራምዱትን አመለካከት ለመታገል ያለመ ማህበር ትናንት በርሊን ውስጥ ተመስርቷል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ