1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር መግለጫ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 17 2011

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ሚንሥትር መሥሪያ ቤቱ፦የኢትዮ ኤርትራ ድንበርን አስመልክቶ ዝርዝር ጉዳዮችን ባይናገርም፦ «ከኢትዮ ኤርትራ ጋር ያለው ኹኔታ በውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር በኩል ምንም አይነት የተለየ ነገር እንደሌለ» ገልጧል።

https://p.dw.com/p/3HRqy
Äthiopien | Außenministerium | Pressekonferenz
ምስል S. Muchie

የውጭ ጉዳይ መግለጫ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ሚንሥትር መሥሪያ ቤቱ፦የኢትዮ ኤርትራ ድንበርን አስመልክቶ ዝርዝር ጉዳዮችን ባይናገርም፦ «ከኢትዮ ኤርትራ ጋር ያለው ኹኔታ በውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር በኩል ምንም አይነት የተለየ ነገር እንደሌለ» ገልጧል። ስለ ሱዳን ወቅታዊ ኹኔታ፤ ኹለተኛው የቻይና የአንድ መቀነት የአንድ መንገድ ፎረም» ብሎም ኢትዮጵያ 26ኛውን የፕሬስ ነጻነት ቀን እንድታዘጋጅ ስለመመረጧ፤ እንዲኹም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ዜጎች ከታንዛኒያ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ ስለተመለሱ ዜጎች ማብራሪያ ተሰጥቷል። ጋዜጣዊ መግለቻውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ኢትዮጵያ  ኤርትሪያ የምትዋሰንባቸው ድንበሮች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁለቱን ሃገሮች የድንበር የሰዎች ዝውውር እና የንግድ ትስስር ተቋማዊ መሰረት ለማስያዝ እየተሰራ ያለው ስራ በመልካም ሁኔታ እየሄደ ነው ከማለት የዘለለ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም፡፡የሱዳንን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተም የተለየ ነገር እንደሌለ እና ነገሩን እንደ አንድ ጎረቤት ሃገር ከብሀሄራዊ ጥቅም አንጻር ክትትል እናደርግበታለን በማለት ቃል አቀባዩ አቶ ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል፡፡ዛሬ የሚጀመረው 2ኛው የቻይና የ 1 መቀነት 1 መንገድ ፎረም ላይም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመራው ልኡክ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያደርግ ፡ ከፎረሙ ሃገሪቱ ተጠቃሚ እንደነበረች በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ከዜጎች ዲፕሎማሲ አንጻርም ታንዛኒያ እና የመን በእስር ላይ የነበሩ ከ 2 መተቶ በላይ እስረኞች ተፈትተው ወደ ሃገር መምጣታቸውንና ፡ በሳውዲ አረቢያ ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 850 ዜጎች በራሳቸው ፈቃድ መመለሳቸውንም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አትቷል፡፡

ሰለሞን ሙጬ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ