1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ወቅታዊ መግለጫ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 20 2013

የኢትዮጵያ መንግሥት ከበለፀጉት አገራት የሚመጣ የሰብአዊ ርዳታን ምንጊዜም የሚፈልግ ቢሆንም የአሰጣጥ ሂደቱ ግን ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆን እንዳለበት መናገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስታት ገለፀ።

https://p.dw.com/p/3zW8q
Äthiopien | Dina Mufti, Sprecher vom Außenministerium
ምስል Solomon Muche/DW

ከብሔራዊ ደህንነት ጋር የተጣጣመ ሊሆን ይገባል

የኢትዮጵያ መንግሥት ከበለፀጉት አገራት የሚመጣ የሰብዓዊ ርዳታን ምንጊዜም የሚፈልግ ቢሆንም የአሰጣጥ ሂደቱ ግን ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆን እንዳለበት መናገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስታት ገለፀ። መንግሥት ይህንን አቋም ያንፀባረቀው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላይ ካደረጉ የረጂ አገራት አምባሳደሮች ጋር ሲወያይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቱ  በሳምንታዊ መግለጫቸው ተናግረዋል። ሌሎች ጉዳዮችንም አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። 

በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ዘልቆ በመግባት በፈፀመው ጥቃት እስካሁን 3.5 ሚሊዮን ህዝብ ለጉዳት ተዳርገው 500 ሺህ ያህል ዜጎች ተፈናቅለዋል ተብሏል። ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ንብረቶችን ማውደሙንም ቀጥሎበታል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተም የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኮንጎ የሚጠራው ስብሰባ እየተጠበቀ መሆኑንና ውይይቱ ሲጠራ ድርድሩ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ