1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለሙ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍ/ቤት ዓመታዊ ጉባኤና አፍሪቃ

ዓርብ፣ ኅዳር 10 2008

ብቸኛው ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ አህጽሮት «ICC» ትኩረቱን ያለማቋረጥ በአፍሪቃውያን ላይ አድርጓል ሲል የአፍሪቃ ኅብረት በፈራሚ ሀገራት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ቁጣውን ገልጿል።

https://p.dw.com/p/1H9jD
Internationaler Strafgerichtshof mit Logo

የአፍሪቃ ኅብረት በኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ «ICC» ያቀረበውን ክስ ውድቅ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል። ም/ቤቱ በአፍሪቃ አህጉር ጠንካራ ድጋፍ እንደተቋቋመ አሁን ግን ሁሉንም በእኩል ዓይን የማያይ ተቋም ሆኖአል ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአፍሪቃ ኅብረት ስም ተናግረዋል። የአፍሪቃ ኅብረቱን ቅራኔ አስመልክቶ የብራስልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።


ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ